Tsehai Publishers
Hi Guest !
Account
  • Welcome, Please Sign In or Register !
  • If You a returning customer

    Sign In

    Password forgotten? Click here.

  • If You a new customer

    By creating an account at Tsehai Publishers you will be able to shop faster, be up to date on an orders status, and keep track of the orders you have previously made.

    Continue

0
Cart
  • Your shopping cart is empty!
0
Wishlist
  • No Books are in your Wishlist.
    Click here for help on using your Wish List
  • Home
  • Contact Us
  • Imprints
  • Specials
  • New Books
  • Store

  Biographies & Memoirs » The Revolution and My Reminiscence

The Revolution and My Reminiscence

Click to enlarge

The Revolution and My Reminiscence
አብዮቱና ትዝታዬ

ISBN Code : 978-1-59907-108-4
Author : Fisseha DestaAll books
Language : Amharic | አማርኛ
Pages number : 598
Format : Paperback
Publication date : 09/12/2015

Price : $44.95

Share

  • Print Frindly View
  • Click on the save to download this page as a PDF Document  Download Flyer
  • Notify me of updates this product
  • Write Review
  • Request Product Information
  • Recommend this book to your library
Description
Content
Reviews
Author

አብዮቱና ትዝታዬ
ፍሥሐ ደስታ (ሌ/ኮሎኔል)

የኢትዮጵያ አብዮት ሰፊ፣ ፈጣንና ውስብስብ የነበረ ቢሆንም በግሌ ተካፋይ የነበርኩበትን፣ በዓይኔ ያየሁትንና በማስረጃ ያረጋገጥኳቸውን እውነታዎችን በተቻለ መጠን ከወገናዊነት በፀዳ መልኩ በዚህ መጽሐፍ ለማቅረብ ሞክሬአለሁ። የኔ ምኞትና ፍላጎት እኩልነት፣ የሕግ የበላይነትና ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ አንድነቷና ልዑላዊነቷ የተጠበቀና የበለጸገች አንዲት ኢትዮጵያን ማየት ነው። ዓላማ በመንደር ልጅነት፣ በጎሳና በዘር የሚለወጥ አይደለም። በዚያ የአብዮት ወቅት የተጋረጠብኝን ሴራና ተንኮል በመቋቋም፤ የገባሁትን ቃል ኪዳንና መሃላ ጠብቄ በንጹህ ህሊናና ቅንነት ሃገሬንና ሕዝቤን አገልግያለሁ።

ደርግ በወሰዳቸው በጎ እርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ፤ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ፤ ሙሉ ሃላፊነትን በመውሰድ፤ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

የሰው ልጅ በተለያየ ምክንያት ለተለያየ ተፅእኖ መውደቁ ስለማይቀር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለራስ በማድላት ፍፁም ከወገናዊነት የፀዳ አይሆንም። እኔም ሙሉ በሙሉ ከወገናዊነት ውጭ ነኝ ብዬ ስለማላምን አንባብያን ይህንን በቅን ልቦና እንዲወስዱልኝ እጠይቃለሁ። ከሰው ስህተት አይጠፋምና መጽሐፉን በሚገባ አንብበው በጭፍን ሳይሆን በገምቢ መልኩ የሚሰጡትን ማንኛውንም አስተያየትና ሂስ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ።

ፍሥሐ ደስታ (ሌ/ኮሎኔል)
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ
ም/ፕሬዝዳንት

ማውጫ

  • ምስጋና
  • የአሳታሚውማስታወሻ
  • ግጥም
  • መግቢያ

ክፍል- ፩: ከ1966 በፊትናበኋላየፖለቲካእንቅስቃሴናየደርግአመሠራረት

ምዕራፍ፩: ቅድመ1966 ዓ.ምፖለቲካዊእንቅስቃሴባጭሩ

  • በአፄውመንግሥትላይየተነሱዓመፆች
  • የኢትዮጵያዘመናዊጦርናየፖለቲካእንቅስቃሴው
  • የኢትዮጵያጦርኃይሎችናየፖለቲካእንቅስቃሴ
  • የኢትዮጵያተማሪዎችእቅስቃሴ- በሀገርውስጥናበውጭሀገር
  • በ1960ዎቹበሀገሪቱያጋጠሙመሠረታዊችግሮች

 

ምዕራፍ ፪:የየካቲት አብዮት ከነገሌ እስከ መሿለኪያ

  • የልጅእንዳልካቸውመሾም
  • የ2ኛዙርወታደራዊኮሚቴመቋቋም
  • ሰኔ21 እናየ3ኛዙርወታደራዊአስተባባሪኮሚቴ
  • ኢትዮጵያትቅደም
  • የደርጉውሳኔአሠጣጥ
  • የንዑስደርጎችመቋቋም
  • በአስተባባሪኮሚቴውላይየተነሱየመጀመሪያቅዋሜዎች
  • የልጅሚካኤልእምሩመሾም
  • የነሐሴወርየንጉሡናየሥርዓታቸውመጋለጥ
  • መስከረም2 ቀን1967

ምዕራፍ፫: ደርግርዕስመንግሥትናርዕስብሔርሆነ

  • የለውጥሐዋርያ
  • በአዲሱመንግሥትላይየተነሣውተቃውሞ
  • ጄነራልአማን፣ደርግናየኤርትራጉዳይ
  • ቅዳሜህዳር14 ቀን1967 ዓ.ም
  • አዲስየደርግሊቀመንበርመመረጥ
  • የዕድገትበህብረትየእውቀትናየሥራዘመቻ
  • የኢትዮጵያሕብረተሰብአዊነት
  • የጊዜያዊመማክርትጉባዔ

ምዕራፍ፬: የገጠርንመሬትለሕዝብያደረገውአዋጅናስርነቀልአብዮትመጀመር

  • የፀረአብዮትእንቅስቃሴ 
  • የከተማቦታናትርፍቤት

ክፍል፪: የብሔራዊዲሞክራሲያዊአብዮትፕሮግራምናየሕዝብድርጅትጉዳይጊዜያዊፅ/ቤትመቋቋም

ምዕራፍ፭:ብሔራዊዲሞክራሲያዊአብዮትፕሮግራም

  • የሕዝብድርጅትጉዳይጊዜያዊፅ/ቤትመቋቋም 
  • ከፍተኛየሕዝብአደራጅኮሜቴ
  • የብሔራዊዲሞክራሲያዊአብዮትፕሮግራም
  • የሕዝብደርጅትጉዳይጊዜያዊጽ/ቤትመቋቋምናየፓለቲካድርጅቶች
  • የብሔርብሔረሰብድርጅቶች
  • መኢሶንእናኢሕአፓ
  • የአብዮትመድረክ
  • የሴቶችአስተባባሪኮሚቴ
  • የውይይትክበቦች
  • የኢትዮጵያሠራተኞችአንድነትማህበር(ኢሠአማ) እናአዲሱየሠራተኛሕግ
  • የኢትዮጵያመምህራንማህበር(ኢመማ)
  • የከተማነዋሪዎችማህበራት(ከነማ)
  • የኢሕአፓየገጠርትግል
  • የኢሕአፖየኤኮኖሚአሻጥር 190
  • የኢሕአወሊመቋቋምናየኢሕአፖየከተማሽብርዝግጅት
  • በደርግውስጥየኢሕአፓእንቅስቃሴ

ምዕራፍ፮:የሀገርውስጥናየአካባቢውወቅታዊሁኔታእናሴራበምኒልክቤተመንግሥት

  • በኮ/ል መንግሥቱ ላይ የተካሄደ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ

ምዕራፍ፯: ነጭናቀይሽብር

  • በኮ/ልመንግሥቱላይየተካሄደየግድያሙከራ
  • የደርጉቋሚኮሜቴናፍጥጫው
  • ጥር26 እናኮ/ልመንግሥቱ
  • ኮ/ልመንግሥቱ የደርጉ ሊቀመንበር ሆኑ
  • ቀይሽብር 
  • የአብዮትጥበቃመቋቋም
  • የኢትዮጵያማርክሲስትሌኒኒስትድርጅቶችህብረትመመሥረትናየማጋለጥዘመቻ
  • የመንጥርዘመቻ
  • የመኢሶንቀይሽብር
  • የሠራተኞችቀንዋዜማናዕለቱ(ሜይደይ) 1969
  • የአዘአኮመቋቋም
  • የኢሕአፖነጭሽብርአስከፊእየሆነመምጣት
  • የኢማልድህነጻእርምጃከህዳርእስከመጋቢት1970
  • የቀይሽብርመቆም
  • በነጭናቀይሽብርሽፋንየተከሄዱግድያዎች 
  • በነጭናቀይሽብርየደረሰውጉዳት
  • ኢሕአፓበኤርትራመገንጠልናበሶማሊያወረራየነበረውአቋም

ክፍል፫: የሶማሊያወረራናየአሜሪካንሴራ፣የድርጅቶችሽኩቻናየኢሠፓኦኮመቋቋም

ምዕራፍ፰: የሶማሊያወረራናየአሜሪካንሴራ፣የድርጅቶችሽኩቻናየኢሠፓኦኮመቋቋም

  • ታጠቅናየሚሊሺያሥልጠና
  • የኢትዮ-ሶቭየትህብረትግንኙነት
  • በኢትዮጵያናበሶማሊያመካከልየሶቭየትህብረትየሽምግልናጥረት
  • የደርጉም/ሊቀመንበርየኮ/ልአጥናፉመገደል
  • የመልሶማጥቃት

ምዕራፍ፱:የምሥራቁድልበሰሜንምይደገማል

  • አራተኛውየአብዮትበዓል
  • የብሔራዊአብዮታዊዘመቻናየማዕከላዊፕላንጠቅላይመምሪያመቋቋም
  • መደበኛናየመሠረተትምህርትዘመቻ
  • የድርጅቶችሽኩቻ
  • የሊቀመንበርመንግሥቱማዕከልመሆን
  • የኢሠፓአኮመቋቋም
  • የኢሠፓአኮጉባኤ
  • ለመሆኑኮ/ልመንግሥቱማንናቸው?
  • የሚኒስትሮችምክርቤት
  • የኢትዮጵያአየርመንገድ
  • የኑሮውድነት
  • የኢኮኖሚሁኔታ፤የካሣጥያቄናገለልተኝነት
  • የንጉሡንባለሥልጣናትማስፈታት
  • የኢትዮጵያ፣የሊቢያናየደቡብየመንየሦስትዮሽስምምነት

ክፍል፬: የኢትዮጵያሠራተኞችፓርቲእናየኢትዮጵያዲሞክራሲያዊሪፐብሊክመቋቋምናየደርግየውድቀትዋዜማ

ምዕራፍ፲:የኢሠፓምስረታ

  • የ1977 ድርቅናየሰፈራፕሮግራም
  • የኢሕዲሪምስረታ

ምዕራፍ፲፩: የሕወሓትእንቅስቃሴናፕሮጀክት76

  • ቀይሽብርበትግራይ
  • በ1975 በሕወሓትላይየተካሄደዘመቻ
  • የማርክሲስትሌኒኒስትሊግትግራይ(ማሌሊት) ምስረታ
  • የደህንነትሚኒስትሩ

ምዕራፍ፲፪:የኤርትራችግር፣የሠላሙጥረትናየውጊያውሁኔታ

  • የአልጄሪያ፣ሊቢያናኢራቅጉብኝት
  • ሱዳን፣ኢትዮጵያናየኤርትራጉዳይ
  • በኤርትራየኢሠፓአኮመቋቋምናየቀይኮከብዘመቻ
  • የቀይኮከብዘመቻ(1974 ዓ.ም)
  • ናቅፋናበዓሉግርማ
  • በኤርትራየተካሄዱዘመቻዎች
  • የጄነራልታሪኩዓይኔመገደልናየአፍአበትመደምሰስ

ምዕራፍ፲፫: በትግራይናበኤርትራራስገዞችየአስቸኳይጊዜሁኔታመታወጅ

  • የትግራይመለቀቅ

ክፍል፭: መፈንቅለመንግሥትናየመጨረሻዋራት

ምዕራፍ፲፬:የግንቦት8 መፈንቅለመንግሥት

  • በመንግሥትምክርቤትየተካሄደስብሰባ
  • በብሔራዊዘመቻመምሪያአዳራሽየተካሄደስብሰባ
  • ከመንግሥትምክርቤትየተሰጠመግለጫናየፕሬዝዳንቱወደሃገርመመለስ
  • ኤርትራናመፈንቅለመንግሥቱ
  • የጦርፍርድቤትመቋቋም
  • የመፈንቅለመንግሥቱመነሻምክንያቶች
  • መፈንቅለመንግሥቱናየውጭእጅ
  • መፈንቅለመንግሥቱለምንከሸፈ

ምዕራፍ፲፭:የሰላሙድርድርመጀመር፤የቅይጥኢኮኖሚመታወጅ፣የጦርነቱመግፋትናየመጨረሻዋእራት

  • የሰላሙድርድርመጀመር
  • ወሎግንባር 
  • የሰሜንሸዋግንባር
  • የቅይጥኢኮኖሚመታወጅ
  • የኢትዮጵያዲሞክራሲያዊአንድነትፓርቲ
  • የጉናተራራናየደብረታቦርግንባር
  • የምፅዋበሻዕቢያእጅመውደቅ 513
  • የብሔራዊሸንጎአራተኛመደበኛጉባኤ
  • ዳግምደብረታቦርናየባህርዳርግንባር
  • የባህርዳርግንባር
  • የብሔራዊሸንጎአስቸኳይስብሰባናየመጨረሻውስንብት
  • ሹምሽር
  • አዲሶቹየካቢኔአባላትሹመትናየመጨረሻዋእራት
  • ፕሬዝዳንቱወደስደትአመሩ
  • ሳይጀመርያለቀውየለንደኑድርድር
  • ግዙፉሠራዊትለምንወደቀ!
  • የሽግግርመንግሥትመቋቋም

ማጠቃለያ

  • የደራሲውየሕይወትታሪክ 
  • የምህፃረቃላትመፍቻናየቃላትትርጉም
  • አባሪዝርዝር
  • ዋቢመፃሕፍት
  • መጠቁም

 

“…ኮ/ል መንግሥቱ ጠመንጃቸውን እንዳነገቱ ብቅ ብለው በደንብ ከተመለከቱን በኋላ “ትክክል ነው” ብለው ተመለሱ። የመጡትም ቀደም ብለው ማን መቅረት ማን መገደል እንዳለበት በወሰኑት መሠረት ስህተት እንዳይፈጠር ለማረጋገጥ እንደነበር ግልፅ ነው።
ከጥቂት ቆይታ በኋላ መ መሪያ ወደነበርንበት የስብሰባ አዳራሽ ተጠራን። ወደዚያ ስናመራ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳንን “ባለፈው ጄኔራል አማን ተገደሉ አሁን ደግሞ ሥራቸውን ከሚሰሩበት ቦታ አምጥተን፣ ራሳችን ሾመን እንዴት እኒህ ሽማግሌ [ጄነራል ተፈሪ] ይገደላሉ? ስለዚህ ለመንግሥቱ እንንገራቸው” አልኩትና ተያይዘን ወደቢሯቸው ገባን። እኛም የመጣንበትን ስንነግራቸው “እውነታችሁን ነው” በማለት የውስጥ ስልክ አንስተው ከደወሉ በኋላ መነጋገሪያውን እያስቀመጡ “አዝናለሁ ጓዶች አልቋል” ብለው ነግረውን እያዘንን ወደ ስብሰባው አመራን።
እንደገባን ኮ/ል መንግሥቱ መጥተው “ስለሁኔታው ለጦሩ ማስረዳት ስላለብኝ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳን ከኔ ጋር እንድትሄድ” በማለት ጠየቁ። ኮ/ል ተስፋዬም “በማዛቸው ወታደሮች ፊት እጄን ሰቅዬ ወጥቼ ጦሩን ለማነጋገር ፈጽሞ ሕሊናዬ ሊቀበለው ስለማይችል አልሄድም፤ እንደውም ወደክፍሌ እመለሳለሁ” አለ። እኔም “ከእንግዲህ በዚህ ዓይነት እዚህ ግቢ ለመሥራት ፍላጐት የለኝም እኔም እንደተስፋዬ ወደክፍሌ መመለስ እፈልጋለሁ” አልኩ። መንግሥቱም ሽጉጣቸውን በማውጣት “ይህን እርምጃ ባልወስድ ኑሮ ሁላችንም አልቀን ነበር፤ በድያችሁ ከሆነ ግን ግደሉኝ” በማለት ሽጉጡን ጠረጴዛው ላይ ወረወሩት…”

* * * * * * * * * *

“…የኢሕአፓ ቆራጥነት፣ የመኢሶን የርዕዮተ-ዓለም ብስለትና የደርግ ሀገር ወዳድነት ተጣምሮ አገሪቱን ወደ ላቀ ደረጃ ሊያደርስ ይችል የነበረ ኃይል በአመራሮቹ ስህተት ያለአግባብ እርስ በርሱ ተጨራርሷል።”

* * * * * * * * * *

"ደርግ በወሰዳቸው በጎ እርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ፤ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ፤ ሙሉ ሃላፊነትን በመውሰድ፤ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።"

* * * * * * * * * *

“‘ኢትዮጵያ ትቅደም! ያለምንም ደም!’ ብለን በተነሣን ማግሥት... እነዚያ ለሀገራቸው የለፉትንና የደከሙትን አዛውንቶች መጦር ስንችል ገደልናቸው።”
 

Reviews

Customers who bought this product also purchased

Metsehafe Bahrey

View Add to Cart


ETHIOPIA: The Derg Years

View Add to Cart


Boko Haram

View Add to Cart


Creating the Ethiopian Diaspora

View Add to Cart


Wax and Gold

View Add to Cart


The Emergence and Proliferation of Political Organizations in Ethiopia

View Add to Cart

Related Categories
Biographies & Memoirs
    Categories
    Book Subjects
    Journals
    Amharic Books
    Imprints
    Upcoming Titles
    Featured Titles
    Upcoming Titles

    View All Products

    Authors

    View All Authors

    Social Login
    Please Login with:
    Google translate

    Information
    • About TSEHAI
    • The TSEHAI Brand
    • Journal Subscription
    • Friends of Tsehai
    • Get Involved
    • Career Opportunities
    • Authors Questionnaire
    • Movements Page
    Author's Info
    Fisseha Desta
    Books
    What's New?
    A Disarming Spirit

    View
    Reviews
    Write ReviewWrite a review on this product!
    Quick Find
     
    Use keywords to find the product you are looking for.
    Advanced Search
    Shipping & Returns Privacy Notice Conditions of Use course-adoptions Media-reviews



      Powered by Books
      Home
    • About Us
    • Our Brand
    • Our Books
    • Our Authors
    • Our Journals
      Our Publications
    • Browse by subject
    • Upcoming Titles
    • Featured Titles
    • Journal Subscription
    • JSTOR
    • Imprints
      Publish with us
    • Authors Questionnaire
    • Submission Form
    • Sitemap
    • Contact Us
    • +
      Legal Section
    • Facebook
    • Tumblr
    • Twitter
    • Blog
    • Pinterest
    • Merchandise

    Sign up for our newsletter



    Copyright © 2019 Tsehai Publishers All Rights Reserved.

    Booksone