If You a returning customer
Sign In
Password forgotten? Click here.
If You a new customer
By creating an account at Tsehai Publishers you will be able to shop faster, be up to date on an orders status, and keep track of the orders you have previously made.
Continue
Click to enlarge
The Revolution and My Reminiscence አብዮቱና ትዝታዬ
Price : $44.95
Add to Cart Add to wish list
አብዮቱና ትዝታዬፍሥሐ ደስታ (ሌ/ኮሎኔል)
የኢትዮጵያ አብዮት ሰፊ፣ ፈጣንና ውስብስብ የነበረ ቢሆንም በግሌ ተካፋይ የነበርኩበትን፣ በዓይኔ ያየሁትንና በማስረጃ ያረጋገጥኳቸውን እውነታዎችን በተቻለ መጠን ከወገናዊነት በፀዳ መልኩ በዚህ መጽሐፍ ለማቅረብ ሞክሬአለሁ። የኔ ምኞትና ፍላጎት እኩልነት፣ የሕግ የበላይነትና ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ አንድነቷና ልዑላዊነቷ የተጠበቀና የበለጸገች አንዲት ኢትዮጵያን ማየት ነው። ዓላማ በመንደር ልጅነት፣ በጎሳና በዘር የሚለወጥ አይደለም። በዚያ የአብዮት ወቅት የተጋረጠብኝን ሴራና ተንኮል በመቋቋም፤ የገባሁትን ቃል ኪዳንና መሃላ ጠብቄ በንጹህ ህሊናና ቅንነት ሃገሬንና ሕዝቤን አገልግያለሁ።
ደርግ በወሰዳቸው በጎ እርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ፤ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ፤ ሙሉ ሃላፊነትን በመውሰድ፤ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
የሰው ልጅ በተለያየ ምክንያት ለተለያየ ተፅእኖ መውደቁ ስለማይቀር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለራስ በማድላት ፍፁም ከወገናዊነት የፀዳ አይሆንም። እኔም ሙሉ በሙሉ ከወገናዊነት ውጭ ነኝ ብዬ ስለማላምን አንባብያን ይህንን በቅን ልቦና እንዲወስዱልኝ እጠይቃለሁ። ከሰው ስህተት አይጠፋምና መጽሐፉን በሚገባ አንብበው በጭፍን ሳይሆን በገምቢ መልኩ የሚሰጡትን ማንኛውንም አስተያየትና ሂስ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ።
ፍሥሐ ደስታ (ሌ/ኮሎኔል)የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክም/ፕሬዝዳንት
ማውጫ
ክፍል- ፩: ከ1966 በፊትናበኋላየፖለቲካእንቅስቃሴናየደርግአመሠራረት
ምዕራፍ፩: ቅድመ1966 ዓ.ምፖለቲካዊእንቅስቃሴባጭሩ
ምዕራፍ ፪:የየካቲት አብዮት ከነገሌ እስከ መሿለኪያ
ምዕራፍ፫: ደርግርዕስመንግሥትናርዕስብሔርሆነ
ምዕራፍ፬: የገጠርንመሬትለሕዝብያደረገውአዋጅናስርነቀልአብዮትመጀመር
ክፍል፪: የብሔራዊዲሞክራሲያዊአብዮትፕሮግራምናየሕዝብድርጅትጉዳይጊዜያዊፅ/ቤትመቋቋም
ምዕራፍ፭:ብሔራዊዲሞክራሲያዊአብዮትፕሮግራም
ምዕራፍ፮:የሀገርውስጥናየአካባቢውወቅታዊሁኔታእናሴራበምኒልክቤተመንግሥት
ምዕራፍ፯: ነጭናቀይሽብር
ክፍል፫: የሶማሊያወረራናየአሜሪካንሴራ፣የድርጅቶችሽኩቻናየኢሠፓኦኮመቋቋም
ምዕራፍ፰: የሶማሊያወረራናየአሜሪካንሴራ፣የድርጅቶችሽኩቻናየኢሠፓኦኮመቋቋም
ምዕራፍ፱:የምሥራቁድልበሰሜንምይደገማል
ክፍል፬: የኢትዮጵያሠራተኞችፓርቲእናየኢትዮጵያዲሞክራሲያዊሪፐብሊክመቋቋምናየደርግየውድቀትዋዜማ
ምዕራፍ፲:የኢሠፓምስረታ
ምዕራፍ፲፩: የሕወሓትእንቅስቃሴናፕሮጀክት76
ምዕራፍ፲፪:የኤርትራችግር፣የሠላሙጥረትናየውጊያውሁኔታ
ምዕራፍ፲፫: በትግራይናበኤርትራራስገዞችየአስቸኳይጊዜሁኔታመታወጅ
ክፍል፭: መፈንቅለመንግሥትናየመጨረሻዋራት
ምዕራፍ፲፬:የግንቦት8 መፈንቅለመንግሥት
ምዕራፍ፲፭:የሰላሙድርድርመጀመር፤የቅይጥኢኮኖሚመታወጅ፣የጦርነቱመግፋትናየመጨረሻዋእራት
ማጠቃለያ
“…ኮ/ል መንግሥቱ ጠመንጃቸውን እንዳነገቱ ብቅ ብለው በደንብ ከተመለከቱን በኋላ “ትክክል ነው” ብለው ተመለሱ። የመጡትም ቀደም ብለው ማን መቅረት ማን መገደል እንዳለበት በወሰኑት መሠረት ስህተት እንዳይፈጠር ለማረጋገጥ እንደነበር ግልፅ ነው።ከጥቂት ቆይታ በኋላ መ መሪያ ወደነበርንበት የስብሰባ አዳራሽ ተጠራን። ወደዚያ ስናመራ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳንን “ባለፈው ጄኔራል አማን ተገደሉ አሁን ደግሞ ሥራቸውን ከሚሰሩበት ቦታ አምጥተን፣ ራሳችን ሾመን እንዴት እኒህ ሽማግሌ [ጄነራል ተፈሪ] ይገደላሉ? ስለዚህ ለመንግሥቱ እንንገራቸው” አልኩትና ተያይዘን ወደቢሯቸው ገባን። እኛም የመጣንበትን ስንነግራቸው “እውነታችሁን ነው” በማለት የውስጥ ስልክ አንስተው ከደወሉ በኋላ መነጋገሪያውን እያስቀመጡ “አዝናለሁ ጓዶች አልቋል” ብለው ነግረውን እያዘንን ወደ ስብሰባው አመራን።እንደገባን ኮ/ል መንግሥቱ መጥተው “ስለሁኔታው ለጦሩ ማስረዳት ስላለብኝ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳን ከኔ ጋር እንድትሄድ” በማለት ጠየቁ። ኮ/ል ተስፋዬም “በማዛቸው ወታደሮች ፊት እጄን ሰቅዬ ወጥቼ ጦሩን ለማነጋገር ፈጽሞ ሕሊናዬ ሊቀበለው ስለማይችል አልሄድም፤ እንደውም ወደክፍሌ እመለሳለሁ” አለ። እኔም “ከእንግዲህ በዚህ ዓይነት እዚህ ግቢ ለመሥራት ፍላጐት የለኝም እኔም እንደተስፋዬ ወደክፍሌ መመለስ እፈልጋለሁ” አልኩ። መንግሥቱም ሽጉጣቸውን በማውጣት “ይህን እርምጃ ባልወስድ ኑሮ ሁላችንም አልቀን ነበር፤ በድያችሁ ከሆነ ግን ግደሉኝ” በማለት ሽጉጡን ጠረጴዛው ላይ ወረወሩት…”
* * * * * * * * * *
“…የኢሕአፓ ቆራጥነት፣ የመኢሶን የርዕዮተ-ዓለም ብስለትና የደርግ ሀገር ወዳድነት ተጣምሮ አገሪቱን ወደ ላቀ ደረጃ ሊያደርስ ይችል የነበረ ኃይል በአመራሮቹ ስህተት ያለአግባብ እርስ በርሱ ተጨራርሷል።”
"ደርግ በወሰዳቸው በጎ እርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ፤ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ፤ ሙሉ ሃላፊነትን በመውሰድ፤ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።"
“‘ኢትዮጵያ ትቅደም! ያለምንም ደም!’ ብለን በተነሣን ማግሥት... እነዚያ ለሀገራቸው የለፉትንና የደከሙትን አዛውንቶች መጦር ስንችል ገደልናቸው።”
View All Products
View All Authors
Sign up for our newsletter
Subscribe
Copyright © 2019 Tsehai Publishers All Rights Reserved.