Tiglachin [978-1-59907-801-4]

$39.95 $29.96



Author : Mengistu Hailemariam



ISBN Code : 978-1-59907-801-4
Language : Amharic
Pages number : 514
Format : ፮ በ ፱፤ ምስሎችና ካርታ ያሉት

ትግላችን  |  የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ

ቅፅ አንድ

 

“የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ከተቀጣጠለበት እስከ ተቀለበሰበት ድረስ ያለው ጊዜ ከመሰል ሕዝባዊ አብዮቶች ጋር ስናነፃፅረው በለጋና በአጭር የተቀጨ አብዮት ቢሆንም በአሥራ ሰባት ዓመታት ውስጥ ያደረገውን ፈጣን ጉዞ፣ ያስተናገዳቸውን ሕዝባዊ ተግባሮች፣ የገጠሙትን ፈተናዎችና የጠየቁትን መስዋዕትነት በሦስት ተከታታይ ቅፆች ለማቅረብ ተገድጃለሁ።

የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ መሪ ግለሰቦች የሚመጡና የሚሄዱ አላፊዎች ሲሆኑ ሃገርና ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ናቸው። ይህም ቢሆን በአንድ ታሪካዊ ወቅት መንግሥታት፣ የፖለቲካ ደርጅቶች ወይም ግለሰቦች ያከናወኗቸው ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተግባሮች ማንም ወደደ ጠላ የዚያ ሃገርና ሕዝብ ታሪክ ናቸው።

ትግላችን ስሙ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ አንድ ትውልድ በሙሉ ቀፎው እንደተነካበት የንብ ሠራዊት ተቆጥቶ በመነሳት ገበሬው ከገባርነት፣ የሠራተኛውን መደብ ከምንዳ ባርነት፣ ጠቅላላውን ባተሌ ሠርቶአደር ሕዝብ ከድንቁርና አረንቋና እጅግ አሳፋሪ ከሆነ የዘላለም ድህነት መንጥቆ በማውጣት ራሱንና አገሩን ለመለወጥ በጀመረው ትግል መሪር መስዋዕትነትን ከፍሎ የትግሉን ጣፋጭ ፍሬ ሳይቀምስ፣ አንድነቱንና ሰላሙን ሳያገኝ እንደገና የጨለመበት አሳዛኝ ሕዝብ ልሳን እንጂ አንባቢን በደስታ ለመመሰጥ የተዘጋጀ የሥነፅሁፍ ድግስ አይደለም።

በአብዮት የትግል ጎራ ወይም አሰላለፍ ላይ ብቻ በማተኮር፣ በብቀላ፣ የአጥቂነት ወይም የተከላካይነት ስሜት አጥቅቶኝ በማጋነን ወይም በማቃለል ታሪኩን ላለማዛባት በተቻለኝ መጠን ከራሴ ጋር ታግያለሁ፣ ከህሊናዬም ጋር ተሟግቻለሁ።

ይኸ ትግላችን የተሰኘ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ታሪክ ትምህርት በመስጠቱ ረገድ ስለሚኖረው ፋይዳ ፍርዱን ለአንባቢው እተዋለሁ።”

ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም

የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ፕሬዝዳንት

የአሳታሚው ማስታወሻ

መቅድም

መግቢያ

  • ጥንታዊት ኢትዮጵያ
  • የአክሱማውያን መንግሥትና ሥልጣኔ አነሳስ
  • ኢትዮጵያ በመካከለኛው ዘመን: የአክሱም መንግሥት ፍፃሜና የዛጉዌ መንግሥት አነሳስ 
  • ከዛጉዌ በኋላ የመጡ ሥርወ መንግሥታት የጠበቃቸው ሥራና የገጠሟቸው ፈተናዎች 
  • ኢማም አህመድ ግራኝ የመራው አመፅ፣ የእስላም አገሮችና የፖርቹጋሎች á‰ áŠ¢á‰µá‹®áŒµá‹« ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት 
  • የኦሮሞ ማህበረሰብ ፈለሳና ወረራ  
  • የሥርዓተ አልበኞች መሣፍንት ዘመን 
  • ዘመነ ኢምፔሪያሊዝም  
  • የአውሮፓ የቅኝ ግዛት ኃይሎችና የአካባቢው ባዕዳን ተስፋፊዎች በኢትዮጵያ ላይ  á‹«á‹°áˆ¨áŒ“ቸው ከበባዎችና ብሎም ወረራዎች  
  • የቱርኮች ከበባና ወረራ 
  • የግብፅ መንግሥት ያደረገው ከበባና የሰነዘረው ወረራ 
  • የአውሮፓ መንግሥታት ግብፆችን ተክተው በኢትዮጵያ ላይ ያደረጉት ከበባና ወረራ 
  • የኢጣሊያ መንግሥት ወረራ
  • ድህረ ፋሽስት ኢትዮጵያ 
  • የኢትዮጵያውያን ጀግንነትና አይበገሬ አርበኝነት 

 

ክፍል አንድ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት መቃረቢያ፣ ዋዜማና አጥቢያ  

1. የአብዮቱ መቃረቢያ

2. የአብዮቱ ዋዜማ 

3. የአብዮቱ አጥብያ

 

ክፍል ሁለት

አብዮታዊት ኢትዮጵያ፡ ከትግል ወደ ድል፣ ከድል ወደ ትግል የኢትዮጵያ አብዮተኞች ጉዞ

4. የአብዮቱ ማግሥት

5. ደርግና የልጅ እንዳልካቸው መንግሥት

6. ደርግ ከልጅ ሚካኤል እምሩ መንግሥት ጋር

7. ዘውዱን ለመገርሰስ የተደረጉ የመጨረሻ ዝግጅቶች

8. ደርግና ሌ/ጄነራል አማን ሚካኤል አንዶም

9. ደርግና ሻለቃ ተፈራ ተክለዓብ 

10. ደርግና ሌ/ኮሎኔል አጥናፉ አባተ

11. ደርግና አፄ ኃይለሥላሴ

12. የጉልታዊውን ሥርዓተ ማህበር ላዕላይና ታህታይ መዋቅር ስለማፈራረስ

 

ክፍል ሦስት

መሬት ለአራሹ

13. የገጠሩን የእርሻ መሬት የአርሶ አደሩ ይዞታ የሚያደርገው አዋጅ ጥናትና መሰናዶ

14. እድገት በሕብረት የእውቀትና የሥራ ዘመቻ

15. የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ገበሬዎች የቀበሌ ማህበር ወደ ከፍተኛ ንቃት፣ á‹µáˆ­áŒ…ት፣ ምርትና ማህበራዊ ይዞታ የማሸጋገር  እምርታ

 

ክፍል አራት

የሠራተኛው መደብና የኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ አደረጃጀት

16. የኢትዮጵያ ሠራተኞች መተዳደሪያ ሕግ

17. የሠራተኛው ማህበርና የኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ አደረጃጀት

18. በአብዮታዊት ኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ኢንዱስትሪ

 

ክፍል አምስት

በአብዮታዊት ኢትዮጵያ ለሰላም የተደረጉ ጥረቶች

19. አብዮታዊት ኢትዮጵያን ለማዳን አማራጭ የሌለው መድኃኒት 

20. ድህረ አብዮት ኢትዮጵያ የሰላም ጥረት በኢትዮጵያዊያን መካከል

21. ለኤርትራ ክፍለ ሃገር ችግር ሰላማዊ መፍትሄ ለማግኘት የተደረጉ ጥረቶች

22. ከሶማሊያ ተስፋፊ መንግሥት ጋር ወደ ጦርነት ላለማምራት በድህረ አብዮት ኢትዮጵያ የተደረጉ የሰላም ጥረቶች

 

ክፍል ስድስት

የውጭ ጥቃቶች

23. ከውጭ የተሠነዘሩብን ጥቃቶች አብዛኛዎቹ በጠላቶቻችን ብርታት ሳይሆን በኛ ድክመትና የዋህነት ነው

24. በዳግማዊ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት

25. በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት

26. በአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት

 

ክፍል ሰባት

ሃገርንና አብዮትን የማዳን ጦርነት ዝግጅት

27. የታጠቅ ጦር ሰፈር ምስረታ

28. የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሠራዊት አመሰራረት

29. ሕዝባዊ ሠራዊታችንን ለማስታጠቅ የተደረጉ ጥረቶች

30. የአብዮታዊ የመከላከያ ሠራዊት አስተዳደር

31. የአብዮታዊ የመከላከያ ሠራዊት አደረጃጀት

32. ዓለም ያደነቀው የኢትዮጵያ አብዮታዊ የመከላከያ ሠራዊት ሰልፍ

 

ክፍል ስምንት

ሃገርንና አብዮትን የማዳን ፍልሚያ

33. የሶማሊያን መንግሥት ወራሪ ሠራዊት ጥቃት ለመከላከል በምሥራቅና  á‰ á‹°á‰¡á‰¥ ግምባር አብዮታዊ ሠራዊታችን ያደረገው ትግል

34. በሐረርጌ፣ በባሌና በሲዳሞ ክፍላተሃገር ደጋማ አውራጃዎች ለሰባት ወራት  á‹¨á‰°á‹°áˆ¨áŒˆ የመከላከል ትግል

35. ከሞስኮ ስንመለስ በአገራችን የጠበቁን ሁኔታዎች

36. የኢሕአፓ አደገኛ ሴራ በቆሬ የጦር ግምባር

 

ክፍል ዘጠኝ

ከመከላከል ወደ ማጥቃት

37. ለመልሶ ማጥቃት ውጊያ የተደረጉ መሰናዶዎች

38. ወራሪው የሶማሊያ መንግሥት የጦር ኃይል ሐረርጌን ለመያዝ ያደረገው  á‹¨áˆ˜áŒ¨áˆ¨áˆ» ጥረት

39. የኢትዮጵያ አብዮታዊ ሠራዊት ከመከላከል ወደ ማጥቃት መሸጋገር

 

ክፍል አስር

ማጠቃለያ

40. ያሸነፈው አብዮት ነው!

 

መዘርዝር

  • ከየካቲት 1966 á‹“.ም እስከ መስከረም 1967 á‹“.ም
  • ከመስከረም 1967 á‹“.ም እስከ መስከረም 1968 á‹“.ም
  • ከመስከረም 1968 á‹“.ም እስከ መስከረም 1969 á‹“.ም
  • ከመስከረም 1969 á‹“.ም እስከ መስከረም 1970 á‹“.ም

 

የቃላቶች ትርጉም

ዋቢ መጻሕፍት

መጠቁም

Close window