Us and the Revolution [978-1-59907-078-0]

$34.95 $29.96Author : Fikre-Selassie WogderesISBN Code : 978-1-59907-078-0
Language : AMHARIC
Pages number : 454
Format : Paperback; 6"x9"; Illustrator

በጡረታ እስከተገለልኩበት ጊዜ ድረስ አብዮቱን በግምባር ቀደምትነት ከመሩት የደርግ አባላት ውስጥ አንዱ ነኝ። ደርግ ከመመሥረቱ በፊት በአገራችን የተካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ምን ይመስሉ እንደነበር፣ ደርግ በኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ፣ ፖለቲካዊ ሥልጣንም እንዴትና ለምን ሊይዝ እንደበቃ፣ሥልጣን ከጨበጠ በኋላ ደግሞ መሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ በማምጣት አገራችን ከኋላ ቀርነትና ከድህነት ተላቅቃ የሠለጠነችና የበለጸገች እንድትሆን ያደረገውን ጥረትና የከፈለውን መስዋዕት በቅርብና በዝርዝር አውቃለሁ።

ደርግ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ፖሊሲዎችን ሲነድፍ፣ የተለያዩ ሕጎችን ሲደነግግ፣ ልዩ ልዩ ውሣኔዎችን ሲያስተላልፍ፣ መመሪያዎችንና ትዕዛዞችን ሲያወጣ፣ በብዙዎቹ ስብሰባዎች በመገኘት የድጋፍ ድምጽ ሰጥቻለሁ፤ አፈጻጸማቸውንም ተከታትያለሁ።

በነበረኝ ሥልጣን ምክንያት ከሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስለነበረኝ በየትኛውም አካባቢና መሥሪያ ቤት የተከናወኑ ሥራዎችንና የተፈፀሙ ስህተቶችን ከሞላ ጎደል አውቃለሁ። በዚህ የተነሣ የደርግን ታሪክ የመፃፍ ሃላፊነት እንዳለብኝ ይሰማኛል።

እስረኛ በነበርኩበት ጊዜ በመጽሐፍ መልክ አዘጋጅቼ ለሕዝብ ለማቅረብ ባልችልም ከእስር ከተፈታሁ በኋላ ግን የደርግን ታሪክ ለመጻፍ ተነሳሳሁ። በተበታተነ ሁኔታ የመዘገብኳቸውን ታሪካዊ ክንውኖች በማሰባሰብና በኢትዮጵያ የአብዮት ሂደት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበራቸውን ወዳጆቼንና የሥራ ባልደረቦቼንም በማነጋገር የደርግንና የአብዮቱን ታሪክ ለመመዝገብ ጥረት አደረኩ።

ባልጠበቅኩት ሁኔታ ከእሥር ቤት ከወጣሁ በኋላ አሁን ያለውና በተከታታይ የሚመጡት ትውልዶች የታሪካቸው አካል ስለሆነው የደርግ ታሪክ በከፊልም ቢሆን እንዲያውቁ የተወሰኑ ጉዳዮችን ብቻ የሚተርክ ይህን መጽሐፍ አዘጋጅቻለሁ።

መጽሐፉ በጥድፊያ ሳይሆን በጥንቃቄና በጥልቀት መነበብ አለበት የሚል እምነት አለኝና መልካም ንባብ እንዲሆንልዎ እመኛለሁ።

 

ፍቅረሥላሴ ወግደረስ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር

ምስጋና

የአሳታሚው ማስታወሻ

መግቢያ

ምዕራፍ ፩                                                                                                                                           

የኢትዮጵያ ሕዝብ የኑሮ ሁኔታ በዚያን ጊዜ

የገበሬው የኑሮ ሁኔታ 

የሠራተኛው ክፍል የኑሮ ሁኔታ 

የወታደሩ ክፍል የኑሮ ሁኔታ

ምዕራፍ ፪     

የተለያዩ ኅብረተሰብ ክፍሎች የትግል ታሪክ  

የገበሬው የትግል ታሪክ 

የሠራተኛው የትግል ታሪክ 

የወታደሩ ክፍል የትግል ታሪክ 

የተማረው ኅብረተሰብ ክፍል የትግል ታሪክ 

የተማሪው ኅብረተሰብ ክፍል የትግል ታሪክ 

ምዕራፍ ፫

የ1966ቱ የሕዝብ የተቃውሞ እንቅስቃሴ  

የገዢው መደብ አባላት የሥልጣን ሽኩቻ 

የወታደሩ ክፍል የአመጽ እንቅስቃሴ 

የነገሌው ጦር የአመጽ እንቅስቃሴ 

የሰሜኑ ጦር እንቅስቃሴ 

ኪነታዊ የጦር ክፍሎች አቋም ስለመውሰዳቸው 

ምዕራፍ ፬     

የመጀመሪያው አስተባባሪ ኮሚቴ መመሥረት  

የሁለተኛው አስተባባሪ ኮሚቴ መመሥረት 

ለምን አራተኛ ክፍለ ጦር እንደ ማዕከል ተወሰደ 

የሦስተኛው አስተባባሪ ኮሚቴ (ደርግ) መመሥረት 

ሻለቃ መንግሥቱ የደርግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ 

የዕቅድ ኮሚቴ ተቋቋመ 

ምዕራፍ ፭

ጄነራል አማን አንዶም ኤታማዦር ሹም ሆነው መሾማቸው  

ልጅ እንዳልካቸው ስለመታሠራቸው 

ልጅ ሚካኤል እምሩ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ 

ምዕራፍ ፮     

የንጉሡን አቅም ለማዳከም የተወሰዱ እርምጃዎች  

ንጉሡን ከሥልጣን ለማውረድ የተወሰዱ እርምጃዎች 

ንጉሡ ከሥልጣን መውረዳቸው 

ጄነራል አማን ርዕሰ-ብሔር ሆነው መመደባቸው 

ምዕራፍ ፯

ከተለያዩ ክፍሎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ መቀስቀስ  

የንዑስ ደርጎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ 

የክብር ዘበኛ ንዑስ ደርግ የተቃውሞ እንቅስቃሴ 

የመሐንዲስ ንዑስ ደርግ የተቃውሞ እንቅስቃሴ 

የአርሚ አቪዬሽን ንዑስ ደርግ የተቃውሞ እንቅስቃሴ 

የንዑስ ደርጎች መበተን 

ምዕራፍ ፰

       የለውጥ ሐዋሪያዎች በየመሥሪያ ቤቱ መመደብ  

ደርግ ወደ ታላቁ ቤተ-መንግሥት ስለመዘዋወሩ 

የደርግ አባላት በኮሚቴዎች መደልደል 

ቤተ-መንግሥቶችን ስለመረከባችን 

ምዕራፍ ፱

       ጄነራል አማንና ደርግ እየተቃቃሩ መምጣታቸው  

በኅዳር 14 ቀን 1967 የተካሄደ ሰብሰባ 

በስድሳዎቹ ላይ የተላለፈው አሳዛኝ ውሳኔ 

ጄነራል ተፈሪ በንቲ የአገሪቱ መሪና የደርግ ሊቀመንበር ስለመሆናቸው 

ምዕራፍ ፲

       የዕድገት በኅብረት ዘመቻ ዝግጅት  

ሶሻሊዝምን እንደ ሥርዓት እንዴት ተቀበልን? 

ታላቁ የዘማቾች ሰልፍ ትርዒት 

ወደ ዘመቻ ጣቢያዎች ስምሪት 

አጉል ዕምነት በዘማቾች ላይ ያስከተለው ጉዳት 

የመሬት አዋጅ ዝግጅትና አፈጻጸም 

ከመሬት አዋጅ መታወጅ በፊት የተደረጉ ዝግጅቶች 

የገጠር መሬት አዋጅ ረቂቅ ለደርግ ውሳኔ መቅረብ 

የገጠር መሬት ታሪካዊ አዋጅ መታወጅ 

የከተማ መሬትና ትርፍ ቤት መወረስ 

ምዕራፍ ፲፩

የመሬት ከበርቴዎች በየአካባቢያቸው መሸፈት  

የኢዲዩ መመሥረትና ያካሄደው እንቅስቃሴ 

ምዕራፍ ፲፪

የብሔራዊ አማካሪ ጉባኤ መቋቋምና ያከናወናቸው ተግባራት  

በብሔራዊ ደረጃ የሚከበሩ በዓላት መወሰን 

የሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 

የደርግና የአማካሪው ጉባኤ ግንኙነት መሻከር 

ምዕራፍ ፲፫

የፖለቲካ ድርጅቶችና የጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት መቋቋም ጥያቄ 

የሕዝብ ድርጅት ጊዜያዊ ጽሕፈት ቤት መቋቋም 

የሕዝብ ድርጅት ጽ/ቤት አባላትን መምረጥ 

በድርጅቶች መሀል እንዲሁም ከደርግ ጋር መቃቃር መከሰቱ 

የኢማሌድኅ መመሥረት 

የብሔረሰቦች ጥያቄን አስመልክቶ 

ሌሎች ውይይት የተካሄደባቸው ነጥቦች 

ምዕራፍ ፲፬    

የኢሕአፓ አመሠራረትና የትግል ስልት  

“ፋሺዝም በኢትዮጵያ አለ” ስለመባሉ 

ኢሕአፓና ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል 

ኢሕአፓ ራሱን በይፋ ካሣወቀ በኋላ 

ኢሕአፓ የትግል ስልት ለውጥ አደረገ 

ደርግ “በኢሕአፓ ላይ የጦርነት አዋጅ አወጀ” ስለመባሉ 

ለትጥቅ ትግል በኢሕአፓ የተደረገ ዝግጅት 

በሻለቃ መንግሥቱ ላይ የተካሄደ የግድያ ሙከራ 

በሰንዳፋ የጦር መሣሪያ ዘረፋ 

የግድያው ዘመቻ መፋፋም 

ኢሕአፓ የገደላቸው 

ነጭና ቀይ 

ምዕራፍ ፲፭    

ኢሕአፓ በደርግ ውስጥ የፈጠረው ቀውስ  

ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱን የማስወገድ እንቅስቃሴ 

በጥር 26 ቀን 1969 ታላቅ እመርታ ተወሰደ 

ምዕራፍ ፲፮

የፖለቲካ ድርጅቶች አወዳደቅ  

የመኢሶን የሥልጣን ጉዞና የፖለቲካ ኪሳራ 

የወዝሊግ ውድቀት 

የወዝሊግ አመራር ከባድ ስህተት 

ታይቶ የጠፋው ማሌሪድ 

ከመነሻው ያላማረበት ኢጭአት 

ምዕራፍ ፲፯    

አገራችን በሶማሊያ መወረሯ  

ታጠቅ ጦር ሠፈር 

የእናት አገር ጥሪ መደረግ 

የ“ታጠቅ ጦር ሠፈር” አሰያየም 

የድንኳን ስጦታና ተከላ 

የመገልገያና የመሠረተ ልማት ግንባታ 

ቁሳዊ ዝግጅት 

ምልመላ፣ አሸኛኘትና አቀባበል 

የምልምሎቹ አጠቃላይ ሁኔታ 

የአዲስ አበባ ሕዝብ ተሳትፎ 

ዝግጅትና ስልጠና 

የፖለቲካ ድርጅቶች ተሳትፎ 

ሰንደቅ ዓላማ መስጠትና ወታደራዊ ሰልፍ 

የደርግ አባላት ተሳትፎ 

የሥራ ኃላፊዎችና የጦር አዛዦች 

የወዳጅ መንግሥታት ዕርዳታ 

የታሪክ ግጥምጥሞሽ 

ምዕራፍ ፲፰

ጠላቶቻችን የዘሩትን አጨዱ  

የሶማሊያ ዕጣ 

ሱዳንም ተመሳሳይ ዕጣ ደረሳት 

የሌሎች ጠላቶቻችን ድርሻ 

ምዕራፍ ፲፱    

የእኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሥራዎች በጭልፍታ  

የመሠረተ ልማት ግንባታ መንገድን በሚመለከት 

የኤሌክትሪክ ኃይል ግንባታና የመስመር ዝርጋታ 

ቴሌኮሚኒኬሽንና መገናኛ 

አየር መንገድን ማስፋፋት 

የባቡር መስመር 

ኢንዱስትሪ 

ማዕድን 

ግብርና 

የጣና በለስ ፕሮጄክት 

የኦሞ፣ የዋቤ ሸበሌና የባሮ ወንዞች ፕሮጄክቶች 

ማህበራዊና ባህላዊ ሥራዎቻችን በጥቂቱ 

የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ 

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግንባታ 

የመከላከያ ኢንዱስትሪ ግንባታ 

ኪነጥበብና ባህልን ለማዳበር የተደረገ ጥረት 

የአማርኛ ቋንቋ እየዳበረ መምጣት 

ስፖርትን ለማስፋፋት የተደረገ ጥረት 

 

መደምደሚያ

መጠቁም 

Close window