Tsehai Publishers
Hi Guest !
Account
  • Welcome, Please Sign In or Register !
  • If You a returning customer

    Sign In

    Password forgotten? Click here.

  • If You a new customer

    By creating an account at Tsehai Publishers you will be able to shop faster, be up to date on an orders status, and keep track of the orders you have previously made.

    Continue

0
Cart
  • Your shopping cart is empty!
0
Wishlist
  • No Books are in your Wishlist.
    Click here for help on using your Wish List
  • Home
  • Contact Us
  • Imprints
  • Specials
  • New Books
  • Store

  Biographies & Memoirs » Bachir Yetekeche Rejim Guzo

Bachir Yetekeche Rejim Guzo

Click to enlarge

Bachir Yetekeche Rejim Guzo
ባጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ፡ መኢሶን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ውስጥ

ISBN Code : 978-1-59-907111-4
Author : Andargachew AssegidAll books
Language : Amharic
Pages number : 524
Format : Paperback
Publication date : 04/15/2020

Price : $39.95

Share

  • Print Frindly View
  • Notify me of updates this product
  • Write Review
  • Request Product Information
  • Recommend this book to your library
Description
Content
Reviews
Author

 “ባጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞ፡ መኢሶን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ውስጥ” ለንባብ ከበቃ 20 ዓመታት አልፏል። የሚተርከው የዛሬ 45 ዓመት በኢትዮጵያ ስለተካሄደው የ1966 አብዮትና በሐምሌ 1960 ስለተመሰረተው የመኢሶን ሚና ነው። ይህ የፀሐይን የሕትመት ጥራት ደረጃ በተከተለ መልኩ የተሟላ የአርትኦት ሥራን፣ አዳዲስ ታሪካዊ ፎቶግራፎችን፣ እንዲሁም የደራሲውን አዲስ መግቢያና መጠቁም ያካተተ ነው።

መፅሐፉ መኢሶን ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ነሐሴ 1969 ድረስ ያለውን የመኢሶንን ታሪክና ሚና ይመለከታል። ከ1960 እስከ 1966 በአገር ውስጥና በውጭ በህቡዕ ሲታገል ቆየ። በየካቲት 1966 እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳተፈ። በየካቲት 1967 የታወጀው የመሬት ላራሹ አዋጅ በሥራ እንዲተረጎም ታገለ። ከሚያዝያ 1968 እስከ ነሐሴ 1969 በነበሩት 15 ወራት ውስጥ ከደርጉ ጋር ጊዜያዊ ትብብርን መሥርቶ ሠራ። በነሐሴ 14፣ 1969 ከደርጉ ተለየ።

መፅሐፉ ስምንት ክፍሎች ያሉት ሲሆን በየክፍሉ ሥር በምዕራፎች፣ በአርዕስትና በንዑስ-አርዕስት እየተዘረዘረ የቀረበ ነው። የመጀመሪያው ክፍል ከተማሪ እንቅስቃሴ ወደ ፖለቲካ ድርጅት መቋቋም የተደረገውን ጉዞና የመጀመሪያዎቹን የትግል ዘመናት ይዳስሳል። ሁለተኛው ክፍል የሚያተኩረው በቅድመ-አብዮት ዘመን በነበሩት የመኢሶን/ኢህአፓ ልዩነቶችና የፖለቲካ ትግሎች ላይ ሲሆን ሦስተኛው ክፍል ደግሞ በየካቲት አብዮት መፈንዳት፣ ሂደትና ክንዋኔ ላይ ይመለሳል። የደረሱትን ሁነቶችና ያስከተሏቸውን ውጤቶች በመዋዕለ-ዜና መልክ ለመከተል ይሞክራል። አራተኛው ክፍል በተለይ የሚመለከተው ከንጉሠ-ነገሥቱ መውርድ እስከ የካቲት የመሬት ይዞታ አዋጅ ድረስ የነበሩትን ጉዳዮች ነው። ዋናውም ጥረት ያንን ብዥ ያለ ዘመን ገለጥ ለማድረግ ነው። ክፍል አምስት ከመሬት ይዞታ አዋጅ እስከ መስከረም 1968 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድረስ የነበረውን “የአንድ እርምጃ ወደፊት፣ ሁለት እርምጃዎች ወደኋላ” ታሪክ ሲዘግብ፤ በተለይ የሚያተኩረው እየተደራረቡ ይደርሱ በነበሩት የኃይሎች አሰላለፍ ለውጦችና ትንቅንቆች ላይ ነው። ከዚህም ጋር በተያዘ ሂሳዊ/ገንቢ-ድጋፍ ስለተባለው የመኢሶን መስመር ነው።

ክፍል ስድስት ወደ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም የተደረገውን ጉዞ ያትታል። በሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት መቋቋም ታሪክ ላይ ይመለሳል። ክፍል ሰባት ከጽ/ቤቱ መቋቋም በኋላ መኢሶን ያካሄዳቸውን ትግሎች የሚዘረዝር ነው። በአብዮቱ መግፋትና በተከታታይ በደረሱት የቅልበሳ ሙከራዎች ላይ ተመልሶ የሚተርክ ነው። ክፍል ስምንት የኢትዮጵያ አብዮት መጨንገፍ የጀመረበትን የመጀመሪያ ወቅት ይመለከታል። መኢሶን የትግል ስልት ያደረገበትን የፖለቲካ ምክንያቶች ያቀርባል። በ“ነጭ/ቀይ ሽብር” ጉዳይ ላይ ይመለሳል።

            የአሳታሚው ማስታወሻ 

            ዕውቅና 

            መግቢያ 

            መቅድም  (1991) 

            መግቢያ (1991) 

ክፍል ፩፡ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት (1959 - 1962)                                                                                                

       ምዕራፍ ፩፡ ከተማሪ እንቅስቃሴ ወደ ፖለቲካ ድርጅት

ዓይነተኛ የሽግግር ዓመት (1959)

የመኢሶን መመሥረት  

       ምዕራፍ ፪፡ የመጀመሪያዎቹ የትግልና የከፍተኛ ጭቆና ዓመታት

የ1961 ትግልና የመጀመሪያው ወቅት  

1962 - ከፍተኛ የጭቆና ዓመት  

ክፍል ፪፡ የመጀመሪያዎቹ ልዩነቶችና የመስመር ትግሎች (1963 - 1965)

       ምዕራፍ ፩፡ የልዩነቶቹ አጀማመርና ይዘታቸው

የመጀመሪያዎቹ ልዩነቶች  

የሁለተኛው ጠቅላይ ኮሚቴ ስብሰባ ውይይቶችና ውሳኔዎች  

መኢሶንና የ“የአልጀሪያው ቡድን” (አንድ)  

       ምዕራፍ ፪፡ መኢሶን በሁለተኛው ጠቅላይ ኰሚቴ ውሳኔ መሠረት የመጀመሪያው አስተባባሪ ኮሚቴ መመሥረት

መኢሶን ወደ መጀመሪያዎቹ የድርጊት እቅዶች

መኢሶንና የ“አልጀሪያው ቡድን” (ሁለት)  

       ምዕራፍ ፫፡ የመጀመሪያው የሁለት ፈር ትግል ዘመን

የመኢሶንና የ”አልጀሪያው ቡድን” መለያየት  

የመለያያው ደብዳቤ እውነተኛው ልዩነት  

ከሚያዝያ 1963 ደብዳቤ በፊት  

መኢሶንና ሮል/ኢሕአፓ  

ክፍል ፫፡ የአብዮቱ መፈንዳትና መኢሶን (የካቲት 1966 - ነሐሴ 1966)    

       ምዕራፍ ፩፡ ኢትዮጵያ የለውጥ እርጉዝ

የጥገና ለውጥ የተሳነው ንጉሣዊ አገዛዝ  

ኢትዮጵያ የትግሎች መናኸሪያ (1963 - 1965)  

       ምዕራፍ ፪፡ የአብዮቱ ሂደትና መኢሶን    

ያልታሰበው የካቲት?  

የተደረሰበት መኢሶን  

       ምዕራፍ ፫፡ የየካቲት አብዮትና መሪ ያልሆነው “መሪ” መኢሶን

መኢሶን ለጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት (ጊሕመ)  

መኢሶን ለሕዝባዊ ኮሚቴዎች  

የነጐደው የካቲትና ሕዝባዊ ኮሚቴዎች  

የካቲት፣ መኢሶን እና የተራማጆች ሕብረት  

       ምዕራፍ ፬፡ መኢሶንና ደርግ

መኢሶን “በበርታ ግፋ” መስመር  

የካቲትና የሥልጣን ጥያቄ  

ክፍል ፬፡ ከንጉሠ ነገሥቱ መውረድ እስከ የካቲቱ የመሬት አዋጅ  (መስከረም 1967 - የካቲት 1967)     

       ምዕራፍ ፩፡ መኢሶን ከ“በርታ ግፋ”፣ ወደ ሂሳዊ ድጋፍ፣ ወደ ፍጹም ተቃውሞ

ህጋዊነት ያጠረው ደርግና መኢሶን

የጊወመ የመስከረም/ኅዳር የጭቆና እርምጃዎችና መኢሶን  

       ምዕራፍ ፪፡ ጊወመ ከ“ኢትዮጵያ ትቅደም” ወደ “ኢትዮጵያ ሕብረተሰብአዊነት”

ኅዳር 14 - አዋሳኝ ዕለት  

የጊወመ የ“ኢትዮጵያ ሕብረተሰብአዊነት” መስመርና መኢሶን  

       ምዕራፍ ፫፡ መኢሶን ወደ ሂሳዊ ድጋፍ

የኅዳር - ጥር የደርጉ እርምጃዎችና የኃይሎች አሰላለፍ ለውጥ  

በመኢሶን ውስጥ ሁለተኛው ዓቢይ የመስመር ትግል  

ክፍል ፭፡ከመሬት ለአራሹ አዋጅ እስከ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ              

         (የካቲት 1967 - መስከረም 1968)    

       ምዕራፍ ፩፡ መሬት ለአራሹ - ዓቢይ ድል

መኢሶን እና የመሬት ጥያቄ  

መኢሶን ለመሬትና ለዲሞክራሲ  

       ምዕራፍ ፪፡ መሬት፣ አብዮትና ፀረ-አብዮት   

ሁለተኛው ከፍተኛ የኃይሎች አሰላለፍ ለውጥ  

መሬት ለአራሹ፣ ደርግና መኢሶን  

       ምዕራፍ ፫፡ አብዮትና ፀረ-አብዮት ማን? ማንን? (ሐምሌ 1967 - ኅዳር 1968)

የሐምሌ - ነሐሴ 1967 ውጥረቶች  

መስከረም - ኅዳር 1968 ማን? ማንን?

መኢሶንና የነሐሴ 1967 - ኅዳር 1968 የአብዮትና ፀረ-አብዮት ትንቅንቆች  

      

ክፍል ፮፡ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም (ጥቅምት 1968 - ሚያዝያ 1968)                        

       ምዕራፍ ፩፡ ከሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽሕፈት ቤት መቋቋም በፊት

ውሸቱን ከእውነቱ  

ከፍተኛ የሕዝብ አደራጅ ኮሚቴ” እና መኢሶን

       ምዕራፍ ፪፡ ደርጉ ወደ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም 

የታህሣሥ - ሚያዝያ 1968 ድርድሮችና ስምምነቶች  

መኢሶንና የደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም  

መኢሶን፣ ደርጉና የኤርትራ ጥያቄ  

ክፍል ፯፡ መኢሶን የሕዝባዊ ሥልጣን መሠረቶችን በመገንባት ትግል  (ሚያዝያ 1968 - መጋቢት 1969)                                 

       ምዕራፍ ፩፡ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት - የትግል መሣሪያ

የጥያቄው እምብርት - ሕዝባዊ የፖለቲካ ሥልጣን  

መኢሶን እና ሕዝባዊ ድርጅቶች  

       ምዕራፍ ፪፡ የአብዮቱ መግፋትና የቅልበሳ ሙከራዎች   

ሻለቃ ሲሳይ ሀብቴ - ብ/ጀ ጌታቸው ናደው  

ቅድመ - ጥር 1969  

ጥር 26፣ 1969  

ክፍል ፰፡ የኢትዮጵያ አብዮት መጨንገፍ የመጀመሪያ ወቅት  (የካቲት 1969 - ነሐሴ 1969)

       ምዕራፍ ፩፡ ድኅረ ጥር 1969

የጥር 26 ማግሥት አሰላለፎችና ትንቅንቆች  

የሶቭየት ሕብረት መግባትና መኢሶን  

መጋቢት 1969 - የመኢሶን ብሔራዊ ኮንፈረንስ  

       ምዕራፍ ፪፡ አምስት የ“ሕብረትና” የልዩነት ወሮች    

የኢመሌድህ የኢማሌድሕ መፀነስ  

የኢሕአፓን ግድያ ለመቋቋም የተደረገው ትብብር  

የአሰሳው ማግሥት ልዩነቶችና አሰላለፎች  

“ነጭ ሽብር”/“ቀይ ሽብር”  

 

             መደምደሚያ  

            ድህረ ቃል  

            ማጣቀሻ  

            ዋቢ መጻሕፍት  

            ምሕጻረ ቃላት  

            ስለ ደራሲው  

            መጠቁም

 

"ሲጀመር የአብዮት ተሳታፊና ሠሪ ሁኖ የተገኘው [የአብዮቱ ትውልድ] ለኢትዮጵያ ያለውን ህልም፣ ርዕዮተ-ዓለሙን፣ ሕዝባዊ ወገናዊነቱን፣ የፖለተካ ፕሮግራሙንና ፅናቱን ይዞ እንጂ በግብታዊ ለፈነዳው አብዮትና በተከታታይ ለተከናወኑት ከባድ ለውጦች የሚመጥን ድርጅታዊ አቅም፣ ልምድ፣ ተመክሮና ብስለት ኑሮት አልነበረም። [ስለዚህም] ስህተቶችን ለመፈፀም የተጋለጠ ትውልድ ነበር።

መኢሶን ትግሉን የተረዳውና ያቀደው በረጅሙ ቢሆንም በትግሉ ውስጥ የተሸነፈ ድርጅት ነው። ለዚህም መፅሐፉ ባንድ ወገን በአብዮቱ ዓቢይ ወቅቶች የመኢሶን ሥፍራና ሚና፥ መኢሶን በተለያዩ ወቅቶች የቀየሳቸው የትግል ስልቶችና ያካሄዳቸውን ትግሎች፤ በሌላውም ወገን መኢሶን ከአብዮቱ በፊትና በአብዮቱ ዘመን የነበረበትን የፖለቲካና ድርጅታዊ ድክመቶችና ስህተቶች በተለይ የአመራሩ የጋራ ስህተቶች የሚያሳይ የጉዞ ትረካ ነው።

የዛሬው ትውልድ [ደግሞ] ለ40 ዓመታት ያህል የኢትዮጵያ የሆኑና የተከማቹ አዎንታዊና አሉታዊ ተመክሮዎች ባለቤት እና የሁለት አብዮቶችና የሁለት ሪፓብሊክ ሥርዓቶች ምንነት ባለቤት ነው። ከዚህም አንፃር በአብዮቱ ትውልድ የተፈፀሙትን ስህተቶች ላለመድገም የታጨ ትውልድ ነው። እነዚህ በራሳቸው የዛሬውንና መጪውን ትውልድ በለውጦቹና ለለውጦቹ በተከፈሉት መስዋዕትነት ላይ ቁሞ ዕድሉን ብሩህ ለማድረግ እንዲተጋ የሚጠሩት የታሪክ ዕሴቶች ናቸው። ከአብዮቶቹ ትውልድ አሉታዊ ገፅታዎች ራሱን እንዲጠብቅ አጥብቀው የሚያሳስቡት የታሪክ ፀጋዎች ናቸው።"

አቶ አንዳርጋቸው አሰግድ ነሐሴ 27 ቀን 1934 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በተፈሪ መኰንንና በአቃቂ አድቬንቲስት ሚሲዮን ትምህርት ቤቶች ካጠናቀቁ በኋላ አምቦ በሚገኘው የግብርና ሞያ ትምህርት ቤት፣ ከዚያም ዓለማያ የእርሻ ኮሌጅ እና በጀርመን አገር ከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ። በተጨማሪ የሥነ-ፖለቲካ ትምህርት በበርሊን ከተማ ተከታትለዋል።

በቅድመ-አብዮት ዓመታት በአውሮጳ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥ አቶ አንዳርጋቸው ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ሲሆን በተለይ የመኢሶን መሥራች አባልና የአመራሩም አካል በመሆን፣ በ1967 ዓ.ም ደግሞ ከአውሮጳ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የመሬት ይዞታና አስተዳደር ሚኒስቴር ባልደረባ፣ እንዲሁም የየካቲት 66 የፖለቲካ ትምህርት ቤት መምህርና ዳይሬክተር በመሆን በኢትዮጵያ የለውጥ እንቅስቃሴ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ትጫውተዋል።

መኢሶን ቀደም ሲል ከደርግ ጋር መሥርቶት የነበረውን ጊዜያዊ ትብብር በነሐሴ ወር 1969 ዓ.ም ሲያቋርጥ አንዳርጋቸው በመጀመሪያ በሲዳሞ፣ ከዚያም በአዲስ አበባና በጎረቤት አገር ተቀምጠው የድርጅቱን ሥራ በህቡዕ ሲያካሂዱ ከቆዩ በኋላ በ1971 ዓ.ም ወደ ቤልጂየም ለመሰደድ ተገደዱ።

በነሐሴ 1983 ከመኢሶን እስከተሰናበቱበት ጊዜ ድረስ፣ የድርጅቱ ዋና ፀሐፊና የውጭ ልሣኑ የ“ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ” አዘጋጅ ሆነው ሠርተዋል። ከ1982 ጀምሮ በብራስልስ ከተማ ቤልጅየም ከ1992 ጀምሮ ደግሞ በምዕራብና በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች የተለያዩ ሰብዓዊ ድርጅቶች ሥራ አስኪያጅ በመሆን እየሠሩ ይገኛል። 

Reviews

Customers who bought this product also purchased

Abyssinia, 1867-1868

View Add to Cart


Black Ethiopia

View Add to Cart


Society & State in Ethiopian History

View Add to Cart


Socialization and Social Control in Ethiopia

View Add to Cart


Letters from Abyssinia

View Add to Cart


The Emergence and Proliferation of Political Organizations in Ethiopia

View Add to Cart

Related Categories
Biographies & Memoirs
    Categories
    Book Subjects
    Journals
    Amharic Books
    Imprints
    Merchandise
    Featured Titles
    Upcoming Titles
    Featured Titles
    Upcoming Titles

    View All Products

    Authors

    View All Authors

    Google translate

    Information
    • About TSEHAI
    • The TSEHAI Brand
    • Journal Subscription
    • Friends of Tsehai
    • Get Involved
    • Career Opportunities
    • Authors Questionnaire
    • Ethiopian Church Art
    Author's Info
    Andargachew Assegid
    Andargachew Assegid 's bio
    Books
    What's New?
    Ethiopian Church Art [Paperback]

    View
    Reviews
    Write ReviewWrite a review on this product!
    Quick Find
     
    Use keywords to find the product you are looking for.
    Advanced Search
    Shipping & Returns Privacy Notice Conditions of Use course-adoptions Media-reviews



      Powered by Books
      Home
    • About Us
    • Our Brand
    • Our Books
    • Our Authors
    • Our Journals
      Our Publications
    • Browse by subject
    • Upcoming Titles
    • Featured Titles
    • Journal Subscription
    • JSTOR
    • Imprints
      Publish with us
    • Authors Questionnaire
    • Submission Form
    • Sitemap
    • Contact Us
      Legal Section
    • Facebook
    • Tumblr
    • Twitter
    • Blog
    • Pinterest
    • Merchandise

    Sign up for our newsletter



    Copyright © 2023 Tsehai Publishers All Rights Reserved.