If You a returning customer
Sign In
Password forgotten? Click here.
If You a new customer
By creating an account at Tsehai Publishers you will be able to shop faster, be up to date on an orders status, and keep track of the orders you have previously made.
Continue
Click to enlarge
The Revolution and My Reminiscence አብዮቱና ትዝታዬ
Price : $44.95
Add to Cart Add to wish list
የኢትዮጵያ አብዮት ሰፊ፣ ፈጣንና ውስብስብ የነበረ ቢሆንም በግሌ ተካፋይ የነበርኩበትን፣ በዓይኔ ያየሁትንና በማስረጃ ያረጋገጥኳቸውን እውነታዎችን በተቻለ መጠን ከወገናዊነት በፀዳ መልኩ በዚህ መጽሐፍ ለማቅረብ ሞክሬአለሁ። የኔ ምኞትና ፍላጎት እኩልነት፣ የሕግ የበላይነትና ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ አንድነቷና ልዑላዊነቷ የተጠበቀና የበለጸገች አንዲት ኢትዮጵያን ማየት ነው። ዓላማ በመንደር ልጅነት፣ በጎሳና በዘር የሚለወጥ አይደለም። በዚያ የአብዮት ወቅት የተጋረጠብኝን ሴራና ተንኮል በመቋቋም፤ የገባሁትን ቃል ኪዳንና መሃላ ጠብቄ በንጹህ ህሊናና ቅንነት ሃገሬንና ሕዝቤን አገልግያለሁ። ደርግ በወሰዳቸው በጎ እርምጃዎች እንደምደሰት ሁሉ፤ በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ፤ ሙሉ ሃላፊነትን በመውሰድ፤ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
የሰው ልጅ በተለያየ ምክንያት ለተለያየ ተፅእኖ መውደቁ ስለማይቀር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለራስ በማድላት ፍፁም ከወገናዊነት የፀዳ አይሆንም። እኔም ሙሉ በሙሉ ከወገናዊነት ውጭ ነኝ ብዬ ስለማላምን አንባብያን ይህንን በቅን ልቦና እንዲወስዱልኝ እጠይቃለሁ። ከሰው ስህተት አይጠፋምና መጽሐፉን በሚገባ አንብበው በጭፍን ሳይሆን በገምቢ መልኩ የሚሰጡትን ማንኛውንም አስተያየትና ሂስ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ።
ፍሥሐ ደስታ (ሌ/ኮሎኔል)
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ም/ፕሬዝዳንት
“…ኮ/ል መንግሥቱ ጠመንጃቸውን እንዳነገቱ ብቅ ብለው በደንብ ከተመለከቱን በኋላ “ትክክል ነው” ብለው ተመለሱ። የመጡትም ቀደም ብለው ማን መቅረት ማን መገደል እንዳለበት በወሰኑት መሠረት ስህተት እንዳይፈጠር ለማረጋገጥ እንደነበር ግልፅ ነው።
ከጥቂት ቆይታ በኋላ መጀመሪያ ወደነበርንበት የስብሰባ አዳራሽ ተጠራን። ወደዚያ ስናመራ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳንን “ባለፈው ጄኔራል አማን ተገደሉ አሁን ደግሞ ሥራቸውን ከሚሰሩበት ቦታ አምጥተን፣ ራሳችን ሾመን እንዴት እኒህ ሽማግሌ [ጄነራል ተፈሪ] ይገደላሉ? ስለዚህ ለመንግሥቱ እንንገራቸው” አልኩትና ተያይዘን ወደቢሯቸው ገባን።
እኛም የመጣንበትን ስንነግራቸው “እውነታችሁን ነው” በማለት የውስጥ ስልክ አንስተው ከደወሉ በኋላ መነጋገሪያውን እያስቀመጡ “አዝናለሁ ጓዶች አልቋል” ብለው ነግረውን እያዘንን ወደ ስብሰባው አመራን። እንደገባን ኮ/ል መንግሥቱ መጥተው “ስለሁኔታው ለጦሩ ማስረዳት ስላለብኝ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳን ከኔ ጋር እንድትሄድ” በማለት ጠየቁ። ኮ/ል ተስፋዬም “በማዛቸው ወታደሮች ፊት እጄን ሰቅዬ ወጥቼ ጦሩን ለማነጋገር ፈጽሞ ሕሊናዬ ሊቀበለው ስለማይችል አልሄድም፤ እንደውም ወደክፍሌ እመለሳለሁ” አለ። እኔም “ከእንግዲህ በዚህ ዓይነት እዚህ ግቢ ለመሥራት ፍላጐት የለኝም እኔም እንደተስፋዬ ወደክፍሌ መመለስ እፈልጋለሁ” አልኩ። መንግሥቱም ሽጉጣቸውን በማውጣት “ይህን እርምጃ ባልወስድ ኑሮ ሁላችንም አልቀን ነበር፤ በድያችሁ ከሆነ ግን ግደሉኝ” በማለት ሽጉጡን ጠረጴዛው ላይ ወረወሩት…”
ፍስሃ ደስታ (ሌ/ኮሎኔል) ከመስከረም 1979 እስከ 1983 የህዝባዊት ዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የገለገሉት ሌ/ኮሎኔል ፍስሃ ደስታ የተወለዱት መጋቢት 24 1933 በአደዋ ከተማ ትግራይ ውስጥ ነበር። በወጣትነታቸው በወቅቱ ዝነኛ በነበረው የሐረር ጦር ትምህርት ቤትና ባሜሪካ ሀገር ከፍተኛ የመረጃ መኮንንነት ሰልጠና ወስደዋል። በክቡር ዘበኛ ውስጥ ከ1956 - እስከ 1963 አገልግለዋል። የ 1966ቱ ኢትዮጵያ ሕዝባች አብዮት ሲፈነዳም የግዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ወስጥ አስተዳደር ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ፣ እንዲሁም በ 1979 የ ኢሠፓ ቁጥጥር ኮሚቴ ፀሐፊ ና የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው አገልገለዋል ።Fisseha Desta (Lieutenant Colonel) was the vice president of the Peoples’ Democratic Republic of Ethiopia (September 1986- May 1991). He was born Adowa town in Tigray in 1941. He joined the then famous Harar military academy and took advanced intelligence officer training in the USA. He served in the Imperial guard of Haile Selassie until the dawn of the revolution in 1974. He was one of the prominent members of the Provisional Military Administrative Council aka Derg. He started as a deputy chair of the administrative committee of Derg, and later as the Vice President of the Republic.
View All Products
View All Authors
Sign up for our newsletter
Subscribe
Copyright © 2024 Tsehai Publishers All Rights Reserved.