If You a returning customer
Sign In
Password forgotten? Click here.
If You a new customer
By creating an account at Tsehai Publishers you will be able to shop faster, be up to date on an orders status, and keep track of the orders you have previously made.
Continue
Click to enlarge
Us and the Revolution እኛና አብዮቱ
Price : $34.95 $29.96
Add to Cart Add to wish list
“...በሊቀመንበርነት ስብሰባውን የሚመሩት ጄነራል ተፈሪ “የቋሚ ኮሚቴው በዛሬው ቀን የሚወያይበትን ጉዳይ አስመልክቶ የመቶ አለቃ ዓለማየሁ የደርጉ ዋና ፀሐፊ ይገልጽልናል” ብለው ስብሰባው መጀመሩን ካበሰሩ በኋላ ዓለማየሁ በአጀንዳው ላይ አጭር ገለጣ ማድረግ ሲጀምር ስልክ ተደወለ። ስልኩ ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ አጠገብ ስለነበር ወዲያው ቅጭል እንዳለ መነጋገሪያውን በማንሳት ሃሎ አሉ። ከሌላው ጫፍ ማን እንደደወለ አላወቀንም። በኋላ እንደታወቀው ሌ/ኮሎኔል ዳንኤል ነበር የደወለው። ምን እንደተነጋገሩ አልተሰማም። ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻ “እሺ እሺ” ብለው ስልኩን ዘጉት። ስልኩን እንደዘጉ “ይቅርታ ስልኩ የተደወለው ከጎንደር ነው። ጎንደር ውስጥ ችግር አለ። እናንተ ቀጥሉ” ብለው ከጀርባቸው ባለው በር በኩል ውልቅ አሉ። በዚህን ጊዜ ዓለማየሁና ሞገስ ጥርጣሬ የገባቸው መሰለ።ዓለማየሁ ንግግሩን አቋርጦ በመስኮት በኩል ውጭ ውጭዉን መመልከት ጀመረ። ዓይኖቹ አላርፍ አሉ። ግራና ቀኝ ይመለከታል። አጠገቡ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በጥርጣሬ ተመለከተ። ሻምበል ሞገስም በር በሩን ይመለከታል። ከአሁን አሁን አንድ ችግር ይከሰታል የሚል ፍርሃት ያደረበት ይመስላል። ሁሉም የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች ፈርተዋል። እንደፈሩት አልቀረም ሌ/ኮሎኔል መንግሥቱ ከወጡ ሁለት ደቂቃ እንኳን አልሞላም ከበስተጀርባ ባለው ኮሪደር የወታደሮችን እርምጃ ሰማን። ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ በፊት ለፊታችን ባሉት መስኮቶች በኩል ተመለከትን። በዚህን ጊዜ ፍስሐ ደስታ “ተከብበናል” አለ። ወዲያው ሁለቱም በሮች በኃይል ተበረገዱ። ሁላችንም ደነገጥን፣ ቀልባችን ተገፈፈ፣ እጢአችንም የወደቀ መሰለን። ድርቅ ብለን በተቀመጥንበት ቀረን።...”
ፍቅረስላሴ ወግደረስ ከመስከረም ጳጉሜ 5 1979 እስከ ጥቅምት 29 1982 የህዝባዊት ዲሞክራስያዊት ሪፑብሊክ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነበሩ። የተወለዱት አዲስ አበባ ቀጨኔ የሚባል ሰፈር ሲሆን አመቱም ሐምሌ 07 1937 ነበር። በኢትዮጵያ አየር ኃይል ማሰልጠኛ ወጣት ካዴት ካዲት ሆነው በመግባት በ 1955 ዓም የተመረቁ ሲሆን በአሜሪካ ሀገርም ስልጠና ወስደዋል። የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት ሲፈነዳ አየር ሃይልን ወክለው የግዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ አባል ሆኑ። በተለያዩ የስልጣን እርከኖች ሀገራቸወን ያገለገሉት ፍቅረስላሴ የኢሠፓ አደራጅ ኮሚቴ የደርግ ቁአሚ ኮሚቴ አባል ነበሩ። በስልጣን ላይ በነበሩበት ግዜ በተለይም የኢትዮጵያ ታሪክ ለትውልድ በመደርስ መልኩ ተሰንዶ አንደቀመጥ የተለያዩ ጥረቶቼን በማድረጋቸው ይታወቃሉ።
Fikreselassie Wogderess was the prime minister of the Peoples’ Democratic Republic of Ethiopia from September 1987 to November 1989. Fikreselassie was born in a place called ketchene in northern Addis Ababa. He was a graduate of the Imperial Airforce in 1963 and have traveled to the USA for further studies. When the Ethiopian revolution of 1974 started, Fikresilassie found himself in the epicenter when he joined the select committee of low ranking military officials who later became Derg which became the force that took over power. He has served in various positions and responsibilities that included as members of the permanent committee of the Derg. While in power, Fikresilassie is credited for championing the writing and documentation of Ethiopian history for the coming generation.
View All Products
View All Authors
Sign up for our newsletter
Subscribe
Copyright © 2024 Tsehai Publishers All Rights Reserved.