If You a returning customer
Sign In
Password forgotten? Click here.
If You a new customer
By creating an account at Tsehai Publishers you will be able to shop faster, be up to date on an orders status, and keep track of the orders you have previously made.
Continue
Click to enlarge
The Ethiopian Orthodox Church Becomes Autocephalous (Coming soon) የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሀገረተኛነት በኢትዮጵያ
Price : $14.95
Add to Cart Add to wish list
ታሪክ እንደሚያስረዳው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን አጥቢያ ሆና ለ1,600 ዓመታት በላይ ኖራለች። ቤተክርስቲያኗ በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአሌክሳንድርያው ፓትርያርክ በተሾሙት በአቡነ ሰላማ መሪነት ብሔራዊ ቁመና ኖሯት እንደተመሰረተችም የኢትዮጵያና የግብፅ መዛግብት ያመለክታሉ። በሰኔ 21 ቀን 1951 ዓ.ም አቡነ ባስልዮስ ብጹዕ ወቅዱስ ተብለው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ሆነው ሲሾሙ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ የዘለቀው ትግል ፍጻሜ አገኘ።
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በአማኝ ብዛት ተጣምረው ከምትበልጣቸው ከግብጽ: ኮፕቲክ)፣ ከሶሪያ፣ አርመን እና ማላንካር ሲሪያክ (ህንድ) ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ጋር በመሆን የ5ኛውን ክፍለ ዘመን የአሌክሳንድርያንና አንፆኪያን ሊቃነ ጳጳሳት ምሳሌ በመከተል እ.ኤ.አ ግብፆች በ451 ዓ.ም “ተላልፏል” የሚሉትን፤ ግን ደግሞ ማስረጃ ያልተገኘለትን የኬልቄዶን ጉባኤ ውሳኔ አልተቀበለችውም። ሆኖም እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአሌክሳንድርያው ሊቀጳጳስ ሥር ነበረች።
የኢትዮጵያ ታሪክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ ወደዘመናዊው ምዕራፍ ሲሸጋገር ለቤተክርስቲያኗ ይሰጥ የነበረው ትኩረት ተቋረጠ፤ ቤተክርስቲያኗ እና መሪዎቿ ከነበራቸው ማዕከላዊ ሚና ከነአካቴው ተነጠሉ፤ የዕውቀት ጣሪያ መለኪያ የነበሩት ሃይማኖታዊ ክርክሮችም ከምህዳር ድንገት ጠፉ። የተወሳሰበው የዘመናዊ ብሔራዊ መንግሥት እሳቤም ለዘመናት የዳበረውን የህብረተሰቡን መንፈሳዊ ሕይወትና እሴት ወደጎን ገፋው። በሂደቱም በሚሊዮኖች ሕይወት ውስጥ ጉልህ ድርሻ የነበራትና ያላት ብሎም ከተከታዮቿ ማንነትና የዘመናዊነት አመለካከት ጋር በእጅጉ የተቆራኘችው ቤተክርስቲያን በዘመናዊው የኢትዮጵያ ጥናት የሚገባትን ድርሻ ሳታገኝ ቀረች።
መቅድም
የደራሲው ማስታወሻ
ምዕራፍ 1፡ መግቢያ
ምዕራፍ 2፡ ማዕረገ-ጵጵስናን በከፊል ኢትዮጵያዊ የማድረግ ሂደት (1929-35)
ምዕራፍ 3፡ የጣልያን ወረራ (1936-41)
ምዕራፍ 4፡ ጥግ ድረስ የሄደው ማዕረገ-ከፍታ
ምዕራፍ 5፡ ራስን በራስ የማስተዳደር ነፃነትን ማግኘት በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ለውጥ አምጥቷልን?
ዋቢ መጻሕፍት
አባሪ
"ደራሲው በ1951 ዓ.ም በተከናወነው የአቡነ ባስልዮስ ሥርዓተ ፓትርያርክነት ላይ በዲያቆንነት ተሳትፏል። በዚህም ለጉዳዩ የነበረውን ቅርበትና ጥናቱን ለማከናወን ያሳየውን ጽናት ለመረዳ ችያለሁ። ፍለጎትና ጽናት ሁሌም ለተዋጣለት የታሪክ ምርምርና ጽሑፍ መሠረት እንደሚሆኑ የአዱኛ አማኑ የጥናት ውጤት እጅግ በጣም ጥሩ ዋቢ ነው።"
--ዶ/ር ዶናልድ ክራሚ
አቶ አዱኛ አማኑ (ኀዳር 5 ቀን 1931 ዓ.ም. ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም) በቀድሞ ሸዋ ክፍለ ሀገር ጅባትና ሜጫ በተባለው ስፍራ ተወለዱ።የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ት/ቤት በ1952 ዓ.ም አጠናቀቁ። በዚህምቆይታቸው ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እጅ በርካታ ሽልማቶችን ተሸልመዋል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ በወቅቱ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባ ውጤት ቢኖራቸውም ሐረር በሚገኘው የመንፈሳዊ ጉባዔ ት/ቤት ለአራት ዓመታት በመምህርነት አገለገሉ። በኋላም አዲስ አበባ በመመለስበቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ገብተው በ1961 ዓ.ም. በታሪክና ሳይኮሎጂ የትምህርት መስክ በባችለር ዲግሪ ተመረቁ። በዚህን ወቅት ለመመረቂያ ያቀረቡት ጥናት በወቅቱ ታላቅ አክብሮትን ያስገኘላቸው ሲሆን ከሃምሳ ዓመት ብኋላም በዚህ መልኩ በመጽሐፍ ለህትመት ለመብቃት ችሏል።
በህይወት ዘመናቸውም በተለያዩ የሙያ መስኮች ሥልጠናዎች የወሰዱና ሥልጠናም በማዘጋጀት የሠጡ ሲሆን በበርካታ ማህበራዊና ቤተሰባዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከፍተኛና ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።አቶ አዱኛ ተማሪ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዩጵያ ሔራልድና በአያሌ ጋዜጦችናመጽሔቶች በብዕር ስም በመፃፍ ይታወቁም ነበር። በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከዚህ በተለያዩ የሥራ መደቦች በኤክስፐርትነት፣ በተመራማሪነት፣ በመምህርነትና በከፍተኛ ኃላፊነት አገልግለዋል።
ካላቸው ከፍተኛ የማስተማር ፍላጐት የተነሳ ከመደበኛ ሥራቸው በተጓዳኝ ለ35 ዓመታት በአለማያ ኮሌጅ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በአባዲና ሰንደፋ የፖሊስ ኮሌጅ፣ በባንክና ኢንሹራንስ ኢንስቲትዩትና በሐረር መምህራን ማሰልጠኛ በመምህርነትምአገልግለዋል። ጡረታ ከወጡ በኋላም ቢሆን በተለያዩ ጊዚያት ስልጠና በመስጠት ተሳትፈዋል።
አቶ አዱኛ አማኑ ለእውነትና ፍትህ የኖሩ፣ ሀገር ወዳድ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን የሚከታተሉና ጠንቅቀው የሚያውቁ እንዲሁም ታሪክ አንባቢና ተመራማሪ ነበሩ።
View All Products
View All Authors
Sign up for our newsletter
Subscribe
Copyright © 2024 Tsehai Publishers All Rights Reserved.