Ethiopia: The Powder Barrel [978-1-59-907113-8]

$14.95



Author : Debebe Eshetu



ISBN Code : 978-1-59-907113-8
Language : Amharic | አማርኛ
Pages number : 64
Format : Paperback

ኢትዮጵያ፡ የባሩድ በርሜል - የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ (1935 እ.አ.አ)
በሮማን ፕሮቻዝካ
ትርጕም በደበበ እሸቱ

የጊዜውን የቅኝ ገዢዎች መላ ፍንትው ብሎ ያመላከተውንና በዘረኛው ጠበቃ በሮማን ፕሮቻዝካ በ1935 (እ.አ.አ) መግቢያ ላይ በጀርመንኛ ቋንቋ ተደርሶ በኦስትሪያ፣ በዓመቱ መጨረሻ ላይ በለንደን ከተማ በእንግሊዙ ዓለም አቀፍ የዜና አገልግሎት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የታተመው ይህ መጽሐፍ እነሆ በእውቁ ከያኒ ደበበ እሸቱ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተመልሶ ለመጀመሪያ ጊዜ ለንባብ ቀርቧል።

የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ዕትም ላይ የሰፈረው የአሳታሚው መቅድም ጽሑፍ “የመጽሐፉ ደራሲ እስከ 1934 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ የዲፕሎማቲክ ስብሰባዎችና በአውሮፓውያን የቆንስላ ልዩ ፍርድ ቤቶች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሲማጸን የነበረ ጋዜጠኛ ነው” ይለዋል። “የኢትዮጵያን ውስጣዊ አስተዳደር በተመለከተ ያሰፈረው ዘገባ የጦርነቱን መቃረብ ከታማኝ ምንጮች ያረጋገጠ መሆኑን[ም] ያስረዳል። በቅርቡ የታዩትን ወቅታዊ ሁኔታዎች አስመልክቶ ያነሳቸው ነጥቦች ተአማኒ በመሆናቸው ፍራቻውና መላ ምቱ ትኩረት ሊቸራቸው ይገባል።” ሲልም ያስጠነቅቃል።

ጸሐፊው ኢትዮጵያ ላይ ካለው የመረረ ጥላቻና ዘረኝነት በመነሳት “ኢትዮጵያ” የምትባል ሀገርና “አማራ” የሚባል ሕዝብ እንዲጠፉ፤ ኢትዮጵያ በዘር፣ በቋንቋና በሀይማኖት ተከፋፍላ ብትንትኗ እንዲወጣ በከፍተኛ ደረጃ አሲሯል። ከጃፓን ጋር ግንባር የፈጠረች አደገኛ አገር መሆኗን በማስገንዘብም ጥላቻውን በሚገርም ሁኔታ ገልጧል። ወደ ዓለም ማኅበርም (ሊግ ኦፍ ኔሽን) “ይህች ሥልጣኔ ያላያት፣ ዕድገት የምትጠላና የባሪያ ንግድ የምታካሂድ ሀገር አባል ልትሆን አይገባትም፤ ወጣቶቿዋ የሠለጠነው ዓለም በሚቸራቸው የትምህርት ዕድል ተጠቅመው ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የሠለጠነውን ዓለም ለማጥፋት የሚጥሩ ናቸው” የሚል መርዝ የረጨ ክፉ ጠላት ነው።

ከሰማንያ ዓመታት በኋላ ደግሞ በዚህ “በባሩድ በርሜል” ፍንዳታ ያልፈራረሰችና በመላ ምቱም መርዝ ያልጠፋች “ጉደኛ” አገር ዜጎች ለመጀመሪያ ጊዜ የዚህን መጽሐፍ ምስጢር በራሳችን ቋንቋ አንባቢ እንሆናለን።

Close window