Medemer [978-1-59-907204-3]

$24.95



Author : Abiy Ahmed



ISBN Code : 978-1-59-907204-3
Language : Amharic
Pages number : 248
Format : Paperback

መደመር የተሰኘው ይህ መጽሐፍ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚና የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ  የሃገር መምራት ኃላፊነት ላይ ከመጡ በኋላ የጻፉት የመጀመሪያ መጽሐፋቸው ነው።


መጽሐፉ ባለፈው ግማሽ ምዕተ-አመት በሃገራችን ውስጥ ከሌላው አለም እየተዋስን የሞከርናቸው ፖለቲካዊ አስተምህሮዎች የተባለላቸውን ያህል ውጤት ያላመጡበት ምክንያት አንዱ ለኢትዮጵያ ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች እንዲሁም ፖለቲካዊ ምህዳር ባዕድ መሆናቸው እንደሆነ ያስገነዝባል። በይዘቱ ወቅታዊው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምሕዳር ሃገር በቀል እና አዲስ የፖለቲካ አስተምህሮን ለማስተዋወቅ ታሪካዊ፣ ተግባራዊና አመክኔያዊ ገፊ ምክንያቶች እንደሚታዩበት ያስረዳል። 


መደመር ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን፣ ባህሎችንና ልማዶችን ተንተርሶ ሃገራዊ ችግርን የመፍታት አስፈላጊነትን በማንሳት እንደ ሃገር በቀልና አዲስ የፖለቲካ ርዕዮተ-አለማዊ አቅጣጫን ያመላክታል።

ከኢትዮጵያውያን መሠረታዊ ሥሪት የሚነሣ፣ ችግሮቻችንን ሊፈታ የሚችል፣ እኛው እያቃናነውና እያሟላነው የምንሄደው፣ ከዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ፣ ሁላችንንም ሊያግባባና ሊያስተባብር የሚችል አንዳች ሉዓላዊና ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና ያስፈልገናል። በዓለም ላይ የሚቀነቀኑ ፍልስፍናዎችን በመዳሰስ ቁም ነገራቸውን ብቻ እንደ አስፈላጊነቱ እየወሰድን ራሳችን የምንፈትለው ችግር ፈቺ ዕሳቤ ያስፈልገናል።


◊ ◊ ◊


ከበጎው የመደመር ልማዳችን በተቃራኒው በጥላቻ፣ በቂም በቀል እና በጠልፎ መጣል ልምምዳችን ምክንያት ሀገራችንን በዓለም መድረክ ላይ የድህነትና የኋላ ቀርነት ተምሳሌት አድርገናታል። ምድሯ የጦርነትና የደም መሬት፣ ሕዝቦቿም የስደተኞች አብነት እንዲሆኑ አድርገናል። ባለመተባበር፣ ባለመተጋገዝ እና ባለመዋደዳችን ማንነታችንን ለውርደት፣ ሀገራችንን መውጫ ቀዳዳ የሌለው ለሚመስል የጉስቁልናና የትርምስ አዙሪት ዳርገናታል። ይኽ እጅግ አስቸጋሪ መንገድ ሀገራችንን ከገደል አፋፍ ላይ ማድረሱ ሳይበቃ የማንመለስበት የመከራ አዘቅት ውስጥ ሳይጨምረን በፊት ጉዞው መገታት ይኖርበታል። ይኽን ለማድረግ ትክክለኛው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው። ለዚያም ነው መደመር ጊዜያችንን የሚዋጅ ዕሳቤ የሚሆነው።

Close window