Bachir Yetekeche Rejim Guzo [978-1-59-907111-4]

$39.95



Author : Andargachew Assegid



ISBN Code : 978-1-59-907111-4
Language : Amharic
Pages number : 524
Format : Paperback

 “ባጭር የተቀጨ ረጅም ጉዞመኢሶን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ውስጥ” ለንባብ ከበቃ 20 ዓመታት አልፏል። የሚተርከው የዛሬ 45 ዓመት በኢትዮጵያ ስለተካሄደው የ1966 አብዮትና በሐምሌ 1960 ስለተመሰረተው የመኢሶን ሚና ነው። ህ የፀሐይን የሕትመት ጥራት ደረጃ በተከተለ መልኩ የተሟላ የአርትኦት ሥራ፣ አዳዲስ ታሪካዊ ፎቶግራፎችን፣ እንዲሁም የደራሲውን አዲስ መግቢያና መጠቁም ያካተተ ነው።

መፅሐፉ መኢሶን ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ነሐሴ 1969 ድረስ ያለውን የመኢሶንን ታሪክና ሚና ይመለከታል። ከ1960 እስከ 1966 በአገር ውስጥና በውጭ በህቡዕ ሲታገል ቆየ። በየካቲት 1966 እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳተፈ። በየካቲት 1967 የታወጀው የመሬት ላራሹ አዋጅ በሥራ እንዲተረጎም ታገለ። ከሚያዝያ 1968 እስከ ነሐሴ 1969 በነበሩት 15 ወራት ውስጥ ከደርጉ ጋር ጊዜያዊ ትብብርን መሥርቶ ሠራ። በነሐሴ 14፣ 1969 ከደርጉ ተለየ።

መፅሐፉ ስምንት ክፍሎች ያሉት ሲሆን በየክፍሉ ሥር በምዕራፎች፣ በአርዕስትና በንዑስ-አርዕስት እየተዘረዘረ የቀረበ ነው። የመጀመሪያው ክፍል ከተማሪ እንቅስቃሴ ወደ ፖለቲካ ድርጅት መቋቋም የተደረገውን ጉዞየመጀመሪያዎቹን የትግል ዘመናት ይዳስሳል። ሁለተኛው ክፍል የሚያተኩረው በቅድመ-አብዮት ዘመን በነበሩት የመኢሶን/ኢህአፓ ልዩነቶችና የፖለቲካ ትግሎች ላይ ሲሆን ሦስተኛው ክፍል ደግሞ በየካቲት አብዮት መፈንዳት፣ ሂደትና ክንዋኔ ላይ ይመለሳል። የደረሱትን ሁነቶችና ያስከተሏቸውን ውጤቶች በመዋዕለ-ዜና መልክ ለመከተል ይሞክራል። አራተኛው ክፍል በተለይ የሚመለከተው ከንጉሠ-ነገሥቱ መውርድ እስከ የካቲት የመሬት ይዞታ አዋጅ ድረስ የነበሩትን ጉዳዮች ነው። ዋናውም ጥረት ያንን ብዥ ያለ ዘመን ገለጥ ለማድረግ ነው። ክፍል አምስት ከመሬት ይዞታ አዋጅ እስከ መስከረም 1968 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ድረስ የነበረውን “የአንድ እርምጃ ወደፊት፣ ሁለት እርምጃዎች ወደኋላ” ታሪክ ሲዘግብ፤ በተለይ የሚያተኩረው እየተደራረቡ ይደርሱ በነበሩት የኃይሎች አሰላለፍ ለውጦችና ትንቅንቆች ላይ ነው። ከዚህም ጋር በተያዘ ሂሳዊ/ገንቢ-ድጋፍ ስለተባለው የመኢሶን መስመር ነው።

ክፍል ስድስት ወደ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም የተደረገውን ጉዞ ያትታል። በሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት መቋቋም ታሪክ ላይ ይመለሳል። ክፍል ሰባት ከጽ/ቤቱ መቋቋም በኋላ መኢሶን ያካሄዳቸውን ትግሎች የሚዘረዝር ነው። በአብዮቱ መግፋትና በተከታታይ በደረሱት የቅልበሳ ሙከራዎች ላይ ተመልሶ የሚተርክ ነው። ክፍል ስምንት የኢትዮጵያ አብዮት መጨንገፍ የጀመረበትን የመጀመሪያ ወቅት ይመለከታል። መኢሶን የትግል ስልት ያደረገበትን የፖለቲካ ምክንያቶች ያቀርባል። በ“ነጭ/ቀይ ሽብር” ጉዳይ ላይ ይመለሳል።

            የአሳታሚው ማስታወሻ 

            ዕውቅና 

            መግቢያ 

            መቅድም  (1991) 

            መግቢያ (1991) 

ክፍል ፩፡ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት (1959 - 1962)                                                                                                

       ምዕራፍ ፩፡ ከተማሪ እንቅስቃሴ ወደ ፖለቲካ ድርጅት

ዓይነተኛ የሽግግር ዓመት (1959)

የመኢሶን መመሥረት  

       ምዕራፍ ፪፡ የመጀመሪያዎቹ የትግልና የከፍተኛ ጭቆና ዓመታት

የ1961 ትግልና የመጀመሪያው ወቅት  

1962 - ከፍተኛ የጭቆና ዓመት  

ክፍል ፪፡ የመጀመሪያዎቹ ልዩነቶችና የመስመር ትግሎች (1963 - 1965)

       ምዕራፍ ፩፡ የልዩነቶቹ አጀማመርና ይዘታቸው

የመጀመሪያዎቹ ልዩነቶች  

የሁለተኛው ጠቅላይ ኮሚቴ ስብሰባ ውይይቶችና ውሳኔዎች  

መኢሶንና የ“የአልጀሪያው ቡድን” (አንድ)  

       ምዕራፍ ፪፡ መኢሶን በሁለተኛው ጠቅላይ ኰሚቴ ውሳኔ መሠረት የመጀመሪያው አስተባባሪ ኮሚቴ መመሥረት

መኢሶን ወደ መጀመሪያዎቹ የድርጊት እቅዶች

መኢሶንና የ“አልጀሪያው ቡድን” (ሁለት)  

       ምዕራፍ ፫፡ የመጀመሪያው የሁለት ፈር ትግል ዘመን

የመኢሶንና የ”አልጀሪያው ቡድን” መለያየት  

የመለያያው ደብዳቤ እውነተኛው ልዩነት  

ከሚያዝያ 1963 ደብዳቤ በፊት  

መኢሶንና ሮል/ኢሕአፓ  

ክፍል ፫፡ የአብዮቱ መፈንዳትና መኢሶን (የካቲት 1966 - ነሐሴ 1966)    

       ምዕራፍ ፩፡ ኢትዮጵያ የለውጥ እርጉዝ

የጥገና ለውጥ የተሳነው ንጉሣዊ አገዛዝ  

ኢትዮጵያ የትግሎች መናኸሪያ (1963 - 1965)  

       ምዕራፍ ፪፡ የአብዮቱ ሂደትና መኢሶን    

ያልታሰበው የካቲት?  

የተደረሰበት መኢሶን  

       ምዕራፍ ፫፡ የየካቲት አብዮትና መሪ ያልሆነው “መሪ” መኢሶን

መኢሶን ለጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት (ጊሕመ)  

መኢሶን ለሕዝባዊ ኮሚቴዎች  

የነጐደው የካቲትና ሕዝባዊ ኮሚቴዎች  

የካቲት፣ መኢሶን እና የተራማጆች ሕብረት  

       ምዕራፍ ፬፡ መኢሶንና ደርግ

መኢሶን “በበርታ ግፋ” መስመር  

የካቲትና የሥልጣን ጥያቄ  

ክፍል ፬፡ ከንጉሠ ነገሥቱ መውረድ እስከ የካቲቱ የመሬት አዋጅ  (መስከረም 1967 - የካቲት 1967)     

       ምዕራፍ ፩፡ መኢሶን ከ“በርታ ግፋ”፣ ወደ ሂሳዊ ድጋፍ፣ ወደ ፍጹም ተቃውሞ

ህጋዊነት ያጠረው ደርግና መኢሶን

የጊወመ የመስከረም/ኅዳር የጭቆና እርምጃዎችና መኢሶን  

       ምዕራፍ ፪፡ ጊወመ ከ“ኢትዮጵያ ትቅደም” ወደ “ኢትዮጵያ ሕብረተሰብአዊነት”

ኅዳር 14 - አዋሳኝ ዕለት  

የጊወመ የ“ኢትዮጵያ ሕብረተሰብአዊነት” መስመርና መኢሶን  

       ምዕራፍ ፫፡ መኢሶን ወደ ሂሳዊ ድጋፍ

የኅዳር - ጥር የደርጉ እርምጃዎችና የኃይሎች አሰላለፍ ለውጥ  

በመኢሶን ውስጥ ሁለተኛው ዓቢይ የመስመር ትግል  

ክፍል ፭፡ከመሬት ለአራሹ አዋጅ እስከ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ              

         (የካቲት 1967 - መስከረም 1968)    

       ምዕራፍ ፩፡ መሬት ለአራሹ - ዓቢይ ድል

መኢሶን እና የመሬት ጥያቄ  

መኢሶን ለመሬትና ለዲሞክራሲ  

       ምዕራፍ ፪፡ መሬት፣ አብዮትና ፀረ-አብዮት   

ሁለተኛው ከፍተኛ የኃይሎች አሰላለፍ ለውጥ  

መሬት ለአራሹ፣ ደርግና መኢሶን  

       ምዕራፍ ፫፡ አብዮትና ፀረ-አብዮት ማን? ማንን? (ሐምሌ 1967 - ኅዳር 1968)

የሐምሌ - ነሐሴ 1967 ውጥረቶች  

መስከረም - ኅዳር 1968 ማን? ማንን?

መኢሶንና የነሐሴ 1967 - ኅዳር 1968 የአብዮትና ፀረ-አብዮት ትንቅንቆች  

      

ክፍል ፮፡ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም (ጥቅምት 1968 - ሚያዝያ 1968)                        

       ምዕራፍ ፩፡ ከሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽሕፈት ቤት መቋቋም በፊት

ውሸቱን ከእውነቱ  

ከፍተኛ የሕዝብ አደራጅ ኮሚቴ” እና መኢሶን

       ምዕራፍ ፪፡ ደርጉ ወደ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም 

የታህሣሥ - ሚያዝያ 1968 ድርድሮችና ስምምነቶች  

መኢሶንና የደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲሞክራቲክ አብዮት ፕሮግራም  

መኢሶን፣ ደርጉና የኤርትራ ጥያቄ  

ክፍል ፯፡ መኢሶን የሕዝባዊ ሥልጣን መሠረቶችን በመገንባት ትግል  (ሚያዝያ 1968 - መጋቢት 1969)                                 

       ምዕራፍ ፩፡ የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት - የትግል መሣሪያ

የጥያቄው እምብርት - ሕዝባዊ የፖለቲካ ሥልጣን  

መኢሶን እና ሕዝባዊ ድርጅቶች  

       ምዕራፍ ፪፡ የአብዮቱ መግፋትና የቅልበሳ ሙከራዎች   

ሻለቃ ሲሳይ ሀብቴ - ብ/ጀ ጌታቸው ናደው  

ቅድመ - ጥር 1969  

ጥር 26፣ 1969  

ክፍል ፰፡ የኢትዮጵያ አብዮት መጨንገፍ የመጀመሪያ ወቅት  (የካቲት 1969 - ነሐሴ 1969)

       ምዕራፍ ፩፡ ድኅረ ጥር 1969

የጥር 26 ማግሥት አሰላለፎችና ትንቅንቆች  

የሶቭየት ሕብረት መግባትና መኢሶን  

መጋቢት 1969 - የመኢሶን ብሔራዊ ኮንፈረንስ  

       ምዕራፍ ፪፡ አምስት የ“ሕብረትና” የልዩነት ወሮች    

የኢመሌድህ የኢማሌድሕ መፀነስ  

የኢሕአፓን ግድያ ለመቋቋም የተደረገው ትብብር  

የአሰሳው ማግሥት ልዩነቶችና አሰላለፎች  

“ነጭ ሽብር”/“ቀይ ሽብር”  

 

             መደምደሚያ  

            ድህረ ቃል  

            ማጣቀሻ  

            ዋቢ መጻሕፍት  

            ምሕጻረ ቃላት  

            ስለ ደራሲው  

            መጠቁም

Close window